ሙሉ ስሙ አሊ መሐመድ ሙሳ ነው፤ በፖስፖርቱም ሆነ በመታወቂያው ላይ ያለው ስም ይኸው ነው ፤ ይህቺ ‹ቢራ› የምትለው ቃል ከመደበኛው የቢራ መጠጥ ጋር ምንም ግንኙነት የላትም፤ ግን የመድረክ ስሙ ሆና ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ መታወቂያው ሆናለች፤
አባቱ አቶ መሐመድ ሙሳ ተምሮ ጥሩ ደረጃ ላይ እንዲደረትስ አልያም ሙያ አውቆ ጥሩ አናጡጢ እንዲሆን ነበር ፍላጎታቸው፤ አሊ ግን በልጅነቱ ጀምሮ በውጡ የሰረፀውን ተሰጥኦውን መነሻ አድርጎ የእንጨት ሳይሆን የኦሮሚኛ ሙዚቃ አናጢ ነው የሆነው፡፡
አሊ ቢራ በሙዚቃ መድረክ ከ50 ዓመታት በላይ ዘልቋል፤ ላበረከተው አስተዋፅኦም ልዩ ልዩ ሽማልማቶችና የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተቀብሏል፡፡ አንጋፋውን የሙዚቃ ሰው ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ ዛሬ እንደወትሮው ማይክ ጨብጦ መድረክ ላይ ለመቆም በማይችልበት ህመም ተሸንፏል፤
ከግማሽ ምእተ ዓመት በላይ የመድረክ ፈርጥ በመሆን እና በአጫዋወት ስልቱ የሚደነቀው አሊ ቢራ ለኦሮምኛ ሙዚቃ ብሎም ለሀገራችን የሙዚቃ እድገት የራሱን ጉልህ አሻራ ያስቀመጠ ሰው ነው፤ አሊ ቢራ አሁን በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ሲሆን እያገገመ ስለመሆኑ የቅርቡ የሙያ ጓደኞቹ ተናግረዋል፡፡
ከሙዚቃ ስራው ጎን ለጎን በበጎ አድራጎት ስራዎቹ የሚታወቀው አሊቢራ ከባለቤቱ ጋር በመሆን በትውልድ አካባባው በድሬዳዋ በርካታ የገጠር ትምህርት ቤቶችን አስገንብቷ፤

