አፍሪካ በዓለም ላይ ካሉ በርካታ የውሳኔ መስጫ ማዕከላት ተገፍታለች አለች- አልጄሪያ

አፍሪካ በዓለም ላይ ካሉ በርካታ የውሳኔ መስጫ ማዕከላት ተገፍታለች – የአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

🇩🇿 በአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በተመድ 80ኛ ጉባዔ የተነሱ ቁልፍ ነጥቦች፦

🔹 ፍልስጤም

➖ እስራኤል በጋዛ ላይ የከፈተችው ጦርነት የዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች በማለት አውግዘዋል።
➖ በ1967ቱ ድንበር ምስራቅ እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ለሚያደርግ የፍልስጤም መንግሥት ድጋፍ ሰጥተዋል።
➖ ፍልስጤም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሙሉ አባል እንድትሆን እና ሕዝቦቿ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
➖ ዓለም አቀፍ ሕግን በመተግበር ላይ የሚታየውን ድርብ መስፈርት ተችተዋል።

🔹 ምዕራብ ሰሃራ

➖ ምዕራብ ሰሃራ በአፍሪካ የመጨረሻዋ ቅኝ ግዛት ናት ብለዋል።
➖ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰሃራዊያን ሕዝብን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲያስከብር ጠይቀዋል።
➖ “የቀጠለውን” የሞሮኮ ወረራ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አውግዘዋል።

🔹 የተባበሩት መንግሥታት ማሻሻያ እና ዓለም አቀፍ ፍትሕ

➖ የተባበሩት መንግሥታት በ80ኛ ዓመቱ ስንኩሉነቱንና ድርብ መስፈርቶችን ማስወገድ አለበት።
➖ አፍሪካ ፍትሐዊ ውክልና እንድታገኝ በፀጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ እንዲደረግ ጥሪ ቀርቧል።

🔹 ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች

➖ በሊቢያ፣ ሱዳን፣ ማሊ እና ሳህል ቀጣና ውስጥ ሰላማዊ መፍትሄዎች እንዲገኙ ተጠይቋል።
➖ የውጭ ጣልቃ ገብነት እና የአፍሪካ “እጀ አዙር-ቅኝ ግዛት” ብዝበዛ ውድቅ ተደርጓል።
➖ ኩባ በአሜሪካ ማዕቀብ ዙሪያ ድጋፍ አግኝታለች፤ በተናጥል የሚጣሉ ማዕቀቦች እንዲያቆሙም ጥሪ ቀርቧል።
➖ ሽብርተኝነት እና ፅንፈኝነት ተወግዘዋል፤ እነሱን ለማጥፋት ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ተጠይቋል።

🔹 ልማት እና ትብብር

➖ በታዳሽ ኃይል፣ በምግብ ዋስትና እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ጎላ ተደርገው ታይተዋል።
➖ ለጋራ ልማት፣ መረጋጋት እና ውህደት “አዲስ የሜዲትራኒያን አጋርነት” የተሰኝ የትብብር ጥሪ ቀርቧል።

🔹 የማጠቃለያ እይታ

➖ አልጄሪያ ከፍልስጤም እስከ ምዕራብ ሰሃራ ከሚገኙ የተጨቆኑ ሕዝቦች እና ከአፍሪካ የለውጥ ጥሪ ጋር በጋራ ተሰልፋለች።
➖ እውነተኛ የባለብዙ ወገን ትብብር እኩልነትን፣ ፍትሕን እና የሕዝቦችን የነፃነትና ክብር መብት መጠበቅ እንደሚጠይቅ ተገልጿል።

Sourcesputnik

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe