አፍሪካ የጋራ መገበያያ ገንዘብ መመሥረት ደቡብ አፍሪካ ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ አስታወቀች

ለአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ግብይት ለሚያገለግለው የጋራ መገበያያ ገንዘብ መመሥረት ደቡብ አፍሪካ ሙሉ ድጋፏን እንደምትሰጥ አስታውቃለች።
የደቡብ አፍሪካ የአለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ናሊዲ ፓንዶር የአፍሪካ ማዕከላዊና ኢንቨስትመንት ባንኮች እንዲሁም የአፍሪካ የገንዘብ ድርጅት መቋቋም አንዱ ምክንያት የአህጉሪቷን ንግድ በአንድ የመገበያያ ገንዘብ ለማሳለጥ ነው ብለዋል።
የመገበያያ ገንዘቡ መመስረት እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑ ይህንን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
ደቡብ አፍሪካም በ1991ዱ የአቡጃ ስምምነት መሰረት የአፍሪካን የንግድ፣ የአገልግሎትና፣ የካፒታል ዝውውሮችን የሚያሳልጡ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ ናት በማለት አስታውቀዋል።
በአፍሪካ ህብረት ስብሰባዎች ላይ ለጋራ መገበያያው ፈጥኖ እውን መሆን የተለያዩ ስራዎችን እንደምትሰራ ነው ያስታወቁት።
የአፍሪካ የገንዘብ ተቋማቱ ለጋራ መገበያያው ወደ ስራ መግባት ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ያሰመሩበት ሚኒስትሯ እነዚህ ተቋማት የአጀንዳ 2063 ፕሮጀክት አካል ናቸውም ማለታቸውን ኒውስ 24 አስነብቧል። (ኢዜአ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe