ኢራን በቅርቡ በነበረው ህዝባዊ አመጽ የተገደሉትን ወደ 3ሺ የሚጠጉ ዜጎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገች፡፡ የኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ይህንን ማድረግ ያስፈለገው ግልጸኝነት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡
የኢራን ፕሬዝዳንታዊ ቢሮ ትላንት በህዝባዊ አመጹ የተገደሉትን ወደ 2ሺ986 ኢራናዊያንን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ የ131 ሰዎች ማንነት ገና እየተጣራ በመሆኑ ዝርዝራቸው ይፋ እንዳልተደረገ የተነገረ ሲሆን አጠቃላይ የሟቾቹ ቁጥር 3ሺ117 ናቸው ተብሏል፡፡
አብዛኛዎቹ ሟቾች ንጹሃን ናቸው የተባለ ሲሆን የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች አሉበትም ተብሏል፡፡ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዜሽኪያን ሁሉም የሞቱት ሴት እና ወንዶች የኢራን ልጆች ናቸው ብለዋል፡፡
ይህ ከፍተኛ የተባለው ህዝባዊ ቁጣ በኢራን የተቀሰቀሰው የዛሬ አንድ ወር ገደማ ነበር፡፡ የቁጣው መነሻ የኑሮ ውድነት ነው ተብሎ የተነረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን የአገዛዝ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠይቁ ድምጾችም ተስተናግደውበት ነበር፡፡
በርግጥ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይህ አመጽ በዋናነት የተቀነባበረው እንደ ሞሳድ ባሉ የውጭ ሃይሎች ነው ብለው ሲከሱ ይደመጣሉ፡፡//

