መርከቡ ከተመደበለት ህጋዊ የጉዞ መስመር ውጪ ሲጓዝ መመታቱን የኢራን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አሜሪካ ለንግግር የሚሆኑ መሰረቶችን በሙሉ አጥፍታቸዋለች አሉ፡፡
ዓለም አሜሪካ የገባቸውን ቃል ትጠብቃለች ብሎ እየጠበቀ በነበረበት ስዓት ጥቃት በመክፈት ለቃሏ እንደማትታመን አሳይታለች ብለዋል፡፡ አሜሪካ ቃሏን ስታጥፍ ለሦስተኛ ጊዜዋ እንደሆነም ቃል አቀባዩ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህ መሠረትም ኢራን የድርድር ይጀመር ጥያቄ ለአሜሪካ አለማቅረቧንም አረጋግጠዋል፡፡
አሜሪካ ኢራን በእየለቱ ወደ ድርድር መመለስ እንደሚገባ እየመለነች ነው ካለች በኋላ ቴህራን ሁኔታውን አስተባብላለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት እስማኤል ባጌህ ቴህራን ጦርነቱን ሊያስቆም የሚችለውና የተቋረጠው ድርደር ዳግም እንዲጀመር ጥያቄ አላቀረበችም ብለዋል፡፡
በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል ያለው ጦርነት ባለፉት ሳምንታት ተባብሶ መጥቶ አሜሪካ በኢራን እጅግ ከባድ የተባሉ ጥቃቶችን ስታደርስ ሰንብታለች፡፡ ቴህራንም በበኩሏ በቀጠናው በሚገኙ ሀገራት የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቅሞች ላይ የአጸፋ ምላሽ ስትሰጥ ቆይታለች፡፡
ከቅዳሜ ወዲህ ጥቃቶች ለጊዜው ጋብ ማለት ማሳየት ጀምረዋል፡፡ ይህም ሁኔታ ተቋርጦ የነበረውን ድርድር ለማስቀጠል እድል ሊኖረው እንደሚችል እየነሳ ነው፡፡

