ኢትዮ ቴሌኮም 3ተኛውን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያ በይፋ አስመረቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ፍየል ቤት ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ያስገነባውን 3ኛውን ዘመናዊ እና ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያ በዛሬው እለት አስመርቋል
የኢኒሼቲቩ መሪ የዲጂታል ሶሉሽን አቅራቢ ከሚለው ራዕይ እና “አዳዲስ ዕድሎችን ማቅረብ” “Bringing New Possibilities” ከሚለው የኩባንያው መርህ ጋር የሚጣጣም የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አንዱ አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ ዘመናዊ የመኪና ኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ በ1 ሰከንድ 1 ኪሎ ሜትር ለመጓዝ የሚያስችል የኤሌክትሪክ ቻርጅ ለማድረግ ሲሆን፣ እንደ ተሸከርካሪው አቅም በ15 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ (100%) የኤሌክትሪክ ኃይል መሙላት ያስችላል፡፡ ሲስተሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ የባትሪ መስፈርቶች እና የደንበኛን ትዕዝዝ ተቀብሎ በመመርመር በተፈለገው መጠን ቻርጅ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ይህ የኤሌክትሪክ መኪና ኃይል መሙያ ጣቢያ በአንድ ጊዜ እስከ 16 ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው በመሆኑ ለአሽከርካሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡ የዚህ ጣቢያ ወደ ሥራ መግባትም፤ ኩባንያው ቀደም ሲል የገነባቸውን ሁለት ጣቢያዎች ጨምሮ በአጠቃላይ በአንድ ጊዜ ለ48 የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎት መስጠት የሚችልበትን አቅም የፈጠረ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የዛሬው 3ተኛው 16 ዲስፔንሮች ያሉት በተመሳሳይ ሰአት 16 መኪኖችን የሚያስተናግድ እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም በቀጣዩ 3 አመታት ውስጥም በበርካታ ከተሞችም ይህ ዘመናዊ እና ፈጣን የኤሌክትሪክ መኪና መሙያ ጣቢያ እንደሚገነባ ተናግረዋል
የቻርጅ ጣቢያው 24/7 አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ በሚገኝ መተግበሪያ ይከናወናል፡፡ ተገልጋዮች አገልግሎቱን ያለማንም አጋዥነት በራሳቸው ማግኘት እና ክፍያቸውንም በቴሌብር ሱአፐርአፕ መፈጸም እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ከዚህ ቀደም በዚሁ አመት በተገነቡት 2ቱ ዘመናዊ የመኪና ኤሌክትሪክ ኃይል መሙያዎች 165 ሺህ የሚደርሱ የኤሌክትሪክ መኪኖች አገልግሎቱን ተጠቅመዋል ተብሏል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe