ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

የኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት አመት 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ ።
 ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 93 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ በዚህም የእቅዱን 103 ነጥብ በመቶ ማሳካት መቻሉ ነው የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፍጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የገለፀት።
የኢትዮ ቴሌኮም የ2016 በጀት አመት አፈፃፀምን በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል። 21 ነጥብ 79 ትርፍ በማስመዝገብም የእቅዱን 108 ነጥብ 7 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተነግሯል።
በበጀት አመቱ የደንበኞቹ ቁጥር 78 ነጥብ 3 ሚሊየን መድረሱን ያስታወቀ ሲሆን በዚህም የእቅዱን 104 በመቶ ማሳካቱ ነው የተገለፀው።
75 ሚሊየን ዜጎች የሞባይል የድምፅ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሲሆኑ 40.4 ሚሊየን ዜጎች ደግሞ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው።
124 ከተሞች የ4ጂ አገልግሎት ማግኘት ሲችሉ 5ጂ አገልግሎትን ደግሞ በ5 ከተሞች ይፋ ማድረግ ተችሏል።
104 ወረዳዎች 3ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። 894ሺሕ መገልገያዎችን ደግሞ ወደ ገበያው ማቅረብ እንደተቻለ ተመላክቷል።
በ2016 ዓ.ም 270 ምርትና አገልግሎት ለደንበኞች የቀረበ ሲሆን 127 አዳዲስ አገልግሎትና 72 የሚሆኑት ደግሞ ማሻሻያ የተደረገባቸው ናቸው።
በቴሌብር አማካኝነትም ኢትዮ ቴሌኮም ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ አገልግሎቶችን ማቅረብ መቻሉን አስታውቋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በአመቱ ውስጥ 732ሺሕ የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረበት ቢሆንም አንዱም ሳይሳካ መቅረቱ ተጠቁሟል።
ከ300ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በኢትዮ ቴሌኮም አማካኝነት የስራ አድል ተፈጥሮላቸዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በሚሰጠው አገልግሎት ከአፍሪካ 2ኛ ከአለም ደግሞ 17ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በመግለጫው ወቅት ተጠቁሟል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe