ኢትዮ ቴሌኮም ዘኔክሰስ የተሰኘ የስልክ ቀፎና አዳዲስ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም ዘኔክሰስ የተሰኘ የስልክ ቀፎና አዳዲስ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች መለያን ይፋ አድርጓል።
ዘኔክሰስ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በቴሌ ክላውድ ብቻ የሚተዳደርና በርካታ መተግበሪያዎች ያሏቸው ዘመናዊ የስልክ ቀፎዎችና ኮምፒውተሮችን ያካተተ ነው።
አዳዲሶቹ የኔክሰስ ምርቶች የ4ኛው ትውልድ ኔትዎርክ የተገጠመላቸውና በተመጣጣኝ ዋጋ ለተገልጋዮች የሚቀርቡ ሲሆን፥ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅዱ በር ከፋች መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በክላውድ ላይ ተመስርተው የሚሰሩት እነዚህ ስማርት መሳሪያዎች የዲጂታል ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እና ሁሉም ዜጋ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተካታች እንዲሆን ለማበረታታት የሚያስችሉ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በዚሁ ወቅት፤ ኩባንያው ያስተዋወቃቸው የዘኔክሰስ ስማርት መሳሪያዎች አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያግዙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽኑን ለማስቀጠል በከተማም ሆነ በገጠር የአገልግሎት ተደራሽነትን፣ የቴሌብርን ዘመናዊ የገበያ መድረክን ጨምሮ በርካታ አበይት የቴሌኮም አገልግሎቶችን ለማጎልበት እየሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ቀደም ሲል እንደ 4ጂ እና 5ጂ፣ ቴሌ ብር፣ ቴሌ ገበያና ሌሎች የዲጂታል አማራጮችን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe