ስማርት ቢሾፍቱ ፕሮጀክት በምዕራፍ ከተማዋን ለማዘመን የሚያስችል የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለው ኢንተርኔት፣ የኦፕቲካል ፋይበር እና ሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት እና የግብር አሰባሰብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማዘመን እንዲሁም አስተማማኝ ደህንነት ያላት ከተማን ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አጽንኦት ተሰጥቷል።
በተጨማሪም ሁሉንአቀፍ የዲጂታል ሶሉሽኖችን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባሻገር ክፍያዎችን በቴሌብር በቀላሉ በማስፈጸም ውጤታማነትን በእጅጉ ለማሳደግ የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም ተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ እና የአኗኗር ዘይቤን ለመቀየር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።
በተለይም ከተማዋን ለቱሪዝም መዳረሻነት፣ ኢንዱስትሪ (Economic zone) እና ኢንቨስትመንት ያላትን ተመራጭነት በማሳደግ ተወዳዳሪነትን እንደሚጨምር እና የቢዝነስ እንቅስቃሴን በማሳለጥ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሻሽል ተገልጿል።

