ኢትዮ ቴሌኮም የሶስተኛ ወገን የመድን አገልግሎትን በቴሌብር የዲጂታል የኢንሹራንስ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ኩባንያው በዛሬው እለት የሶስተኛ ወገን የመድን አገልግሎትን በዲጂታል ስርዓት ለመስጠት የሚያስችል በቴሌብር የዲጂታል የኢንሹራንስ አገልግሎት ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ጋር በመተባበር ይፋ አድርጓል።
የዘመነው የኢንሹራንስ አገልግሎት የ18 ኢንሹራንስ ኩባንያ ደንበኞች የሶስተኛ ወገን የአዲስ ምዝገባ እና የእድሳት ክፍያቸውን በወቅቱ ካሉበት ሆነው በቴሌብር እንዲፈጽሙና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። በተጨማሪም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሥራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የተማከለ መረጃ አያያዝ እንዲኖራቸው፣ የተሟላ ሪፖርት በወቅቱ እንዲያገኙ እንዲሁም ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለደንበኞቻቸው እንዲያቀርቡ ያስችላል ብላል፡፡

