ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪትስ አ.ማ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ አከናዋኝ ድርጅት ስራ መጀመሩን አስታወቀ

ኢትዮ ፊደሊቲ ሴኪዩሪቲስ አ.ማ ከኢትዮጽያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፈቃድ ያገኘው መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ነበር፡፡ አክሲዮን ማህበሩ በተፈረመ ካፒታል ሃምሳ ሚሊዮን ብር፡በተከፈለ አስራት አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ አራት ሺ ብር የተቋቋመ ስለመሆኑ ስራ መጀመሩን ባበሰረበት ወቅት የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አበባው ዘውዴ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ፊደሊቲ በኢትዮጽያ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ የሚያሰልፈውን  የሰነደ መዋለ ገበያ አከናዋኝ ፈቃድ ከካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፈቃድ በማግኘት ነው ወደ ስራ የገባው፡፡

ድርጅቱ ሰነደመዋል መግዛትና መሸጥን እንዲሁም የገበያ ተሳታፊዎችን ማማከር፡ካፒታል ፈላጊ ኩባንያዎችን ከኢንቨስተር ጋር ማገናኘት እና የግብይት አማካሪነትን እንደሚሰራም አቶ አበባው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጽያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ ነው ያለውን የሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ አከናዋኝ አገልግሎት ሰጭዎች መጋቢት 12 /2017 ፈቃድ መስጠቱ ይታወሳል፡፡

የካፒታል ገበያ አማራጭ የቁጠባ መንገዶችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ሚና እንዳለውም በባለሙያዎች ይነገራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የካፒታል ገበያው መጠናከር ላባንኩ ዘርፍም አስተዋጾ እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe