ለኮሮና ቫይረስ የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች 58 አይነት መድሃኒቶች ለኢንስቲትዩቱ አስረከቡ!
የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበር ከኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ይጠቅማሉ ያላቸውን 58 አይነት የባህል መድሃኒቶች ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያስረከቡ ሲሆን ኢንስትቲዩቱ ሳይንሳዊ ምርመራ ማድረግ ጀምሯል።
Read also:በአረንጓዴ አሻራ ከተከተሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ…
ማህበሩ ለበሽታው ፈውስ ሊሰጡ ይችላሉ ያላቸውንና በመጀመሪያ ዙር ወደ ላብራቶሪ ገብተው ተጨማሪ ፍተሻና ምርምር የሚደረግባቸው 25 አይነት ባህላዊ መድሃኒቶችንም በመለየት በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስተባባሪነት ለኢንስቲትዩቱ አስረክቧል፡፡
Read also:የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን ከግለሰብ ቤት አገኘ
ከቀረቡት የባህል መድሃኒቶች ውስጥ በህመሙ ላልተያዙ ሰዎች መከላከያ የሚሆኑ 13 አይነት መድሃኒቶችና በህመሙ ለተያዙ ሰዎች ሊሆኑ የሚችሉ ደግሞ 45 አይነት መድሃኒቶች በጥቅሉ 58 (ሃምሳ ስምንት) አይነት መድሃኒቶች ይገኙበታል፡፡
በዚሁ መሰረት መድሃኒቶቹ በመከላከያ መልክ የቀረቡ፣ በተለያዬ መልክ የሚሰጡና ወደ ሆድ የሚገቡ ተብለው የተከፋፈሉ ሲሆን ከዚህ በፊት በጤና ሚኒስቴር በኩል በተሰጠ መመሪያ መመሰረት በዛሬው ዕለት በምድብ 1 ወደ ላብራቶሪ የሚገቡ መድሃኒቶች ኮድ በማህበሩ የተሰጣቸው ሆነው የቀረቡ ስለሆነ ቀጣይ ምርመራ ይደረግባቸዋል ተብሏል፡፡
Read also:ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ደረጃ የውሃ ሙሌት ለመጀመር የግብፅን ይሁንታ እንደማትፈልግ ለፀጥታው ምክር…
በርክክቡ ላይ የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሂሩት ካሳው እና የባህል ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ ወ/ሮ ብዙነሽ መሰረት የተገኙ ሲሆን የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት ህክምና አዋቂዎች ማህበርን በመወከል የባህል ሀኪም አቶ ታደሰ ወ/ገብርኤል በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪና የባህላዊና ዘመናዊ መድሃኒቶች ምርምር ዳይሬክተር ለሆኑት ለወ/ሮ ፍሬህይወት ተካ ማስረከባቸውን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

