ይህ የተነገረው በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና ሀበሻ ቢራ አብረው የዘለቁበትን የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በይፋ ማደሳቸውን ባስታወቁበትና ባካሄዱት የፊርማ ስምምነት ላይ ነው::
አዲሱ ስምምነት ክለቡን በፋይናንስ አቅም በመደገፍ ጠንካራ ቡድን ለመገንባት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተጠቅሶ ለ3 አመት የ180 ሚሊየን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት አድርገዋል::
በስምምነቱ ወቅት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አመራሮች እንደገለጹት፤ ሀበሻ ቢራ ክለቡ አሁን ለደረሰበት ደረጃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ ግንባር ቀደም ስፖንሰሮች አንዱ ነው።
የሀበሻ ቢራ ዋና ሥራ አስፈፃሚ (CEO) ሚስተር ኦሞ ኦሂዌሬ በበኩላቸው፤ ሀበሻ ቢራ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ላለፉት 12 ዓመታት አብሮ መቆየቱን እና የንግድ ምርቱ (ቢራው) ለገበያ ከመቅረቡ በፊት ጀምሮ ከክለቡ ጋር ጠንካራ ቁርኝት እንደነበረው ገልጸዋል።
በዛሬው የስፖንሰርሺፕ ስምምነትም ኢትዮጵያ ቡና 45 ሚሊዮን ብር የስፓንሰርሺፕ ክፍያ እንደሚያገኝና ከዚህ በተጨማሪ ከቢራ ሽያጭ ላይ የሚሰበሰብ 15 ሚሊዮን ብር በአጠቃላይ 60 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ክፍያ እንደሚያገኝ ተነግሯል።
#ድሬቲዩብ
ኢትዮጵያ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ዋንጫን ካሸነፈ 15 ሚሊየን ብር ሊሸለም ነው

