ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እንዲመጣ ጠየቀች

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ሥሜ፤ የቱርክሜንስታኑ ጉባኤ ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ላይ የእይታ ለውጥ እና ዓለም ለጉዳዩ ያለው ቁርጠኝነት ዳግም ይታደስበታል ብላ እንደምትጠብቅ ተናግረዋል፡፡

“የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ቀጥተኛ የባሕር በር መተላለፊያ ባለማግኘታቸው፣ ከፍተኛ የትራስፖርት ወጪ እና መሠረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላትን ጨምሮ በሌሎች መሠረታዊ ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ” በሦስተኛው የተባበሩት መንግሥታት የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ በንግግራቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ይገኙበታል፦

◻️ የባሕር በር መሠረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ሙሉ ለሙሉ ሊተገበሩ ይገባል፡፡
◻️ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት እኩል የማሪታይም መብታቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
◻️ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ያልተቋረጠ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የባሕር መተላለፊያ የማግኘት መብታቸው ሊከበር ይገባል፡፡
◻️ የባሕር በር የማግኘት መብት ላይ የሚሠሩ ተቋማት ሀገራትን በእኩልነት ማስተናገድ አለባቸው፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የባሕር በር የማግኘት መብታቸውን እውን ማድረግ በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ ሙያዊ ምክረ ሀሳቦችን የሚያቀርብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን መቋቋሙን እንደምታደንቅም ገልፀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ታንዛኒያ ወደብ አልባ ሀገራትን የባሕር በር ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች፡፡ዶዶማ የባሕር በር የሌላቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የዳሬ ሰላምን ወደብ እንዲጠቀሙ ፍላጎት እንዳላትም ገልጻለች፡፡

3ኛው የተመድ የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ጉባዔ ላይ የወደቡን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች ማከናወነ እንደጀመረችም አስታውቃለች፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe