ኢትዮጽያ 100ሺ መምህራን እጥረት እንዳለባታ ተሰማ፡፡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው አንድ ዓመት በፊት እንዲያስተምሩ በማድረግ ነው የመምህራን ባንክ ይጀመራል ሲል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ወጭያቸውንም መንግስት ይሸፍናል ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጽያ ዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ፕሮግራም ከ2019 ዓ.ም ስራ እንደሚውልም ተነግሯል፡፡
ይህም ኢትዮጽያ ከ50 ዓመት በኋላ በድጋሚ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የግዳጅ አገልግሎት ልታሰማራ መሆኑን ያመላክታል፡፤
በወታደራዊው የደርግ መንግስት ዘመን ኢትዮጽያ በ1967 ከ60ሺ በላይ የዩኒቨርሲቲ እና የሃይስኩል ተማሪዎችን የእድገት በህብረት የዕውቅትና የስራ ዘመቻ በሚል አሰማርታ እንደነበር ይታወቃል፡፡ አሁን ገጥሟል የተባለውን የመምህራንን እጥረት ለማቃለል በሚል የዩኒቨርሲቲ ሰርቪስ ሊጀመር መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ አሰራሩ በሀገሪቱ ያለውን የመመህራን ዕጥረት እንደሚቀርፍ አብራርተዋል፡፡
በዚህ ወቀት በሀገሪቱ 100ሺ የሚደርስ የመምህራን እጥረት መኖሩን በተደረግ ግምጋ መታወቁንም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ መሠረት በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ ማህበረሰቡ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ይመረቃል ነው የተባለው፡፡
መምህራን የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ እና ሙያው ላይ የሚታየውን ክፍተት ለማስተካከል ታሳቢ ያደረገ የመምህራን ባንክም ለማቋቋም እቅድ መያዙ ተሰምቷል፡፡

