እስራኤል በ15 ቀናት በፈጸመችው ጥቃት 322 ህጻናት መገደላቸውን ተመድ አስታወቀ፡፡
እስራኤል እንደ አዲስ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በጋዛ በጀመረችው ጥቃት 322 መገደላቸውን የመንግስታቱ ድርጀት ይፋ አድርጓል፡፡
ከዚህ ውጭም ቢያንስ 609 ህጻናት መቁሰላቸውን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ገልጻል፡፡
የጋዛ ተኩስ አቁም ስምምነት ለህጻናቱ የወደፊት ህይወታቸውን የሚያስቀጥል እንዲሁ የማገገምን ተስፋን የከፈተ ነበር ሲሉ የዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ራስል ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ህጻናቱ እንደገና አዙሪቱ ወደማያልቅ አስከፊ ጥቃቶች እንዲገቡ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡
እስራኤል የመጀመሪያው ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነትን መራዘምን ሐማስ እንዲቀበል ትፈልጋለች፡፡ ሐማስ በበኩሉ ሁሉም ታጋቾች እንዲለቀቁ እንዲሁም የእስራኤል ጦር ከጋዛ ሙሉ በሙሉ እንዲወጣ እና ዘላቂ መረጋጋትን ማምጣት ያለመው ሁለተኛው ምዕራፍ ይሁን እያለ ነው፡፡/

