እስራኤል የጋዛ ራፋ ማቋረጫን ዳግም ክፍት ማድረጓ ተሰምቷል፡፡ እስራኤል አሁን ክፍት ያደረገችውን የራፋን ማቋረጫ ከግንቦት 2024 ጀምሮ በቁጥጥሯ ስር አድርጋው ነው የምተገኘው፡፡

ይህ የአሁኑ የድንበር ማቋረጫው መከፈት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የጋዛውን ጦርነት ለመቋጨት የነደፉት የሰለም እቅዱ አንድ አካል መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

እስራኤል ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ነው ፍልስጤማዊያን በእግር ተመልሰው እንዲገቡ በሚል ዳግም ክፍት ያደረገችው ተብሏል፡፡ ምንም እንኳን የድንበር ማቋረጫው ክፍት መሆኑ ቢነገርም  ጥብቅ ቁጥጥር ግን እንደሚደረግበት ታውቋል፡፡

የራፋ ድንበር ማቋረጫ መከፈት የሚለው ነጥብ በፕሬዝዳንት ትራምፕ የሰላም እቅድ ውስጥ በመጀመሪያው ምዕራፍ ውስጥ የተካተተ ነው፡፡

እንደ ፍልስጤማዊያን ባለስልጣናት መረጃ 100ሺ የሚደርሱ ፍልስጤማዊያን የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰ አንስቶ ሸሽተው ወጥተዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ከጋዛ የወጡት በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ 9 ወራቶች ጊዜ ውስጥ ነው ብለዋል፡፡

አሁን የፕሬዝዳንት ትራምፕ የሰላም እቅድ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ሁለተኛውና እጅግ ወሳኝ ወደሆነው ምዕራፍ ተሸጋግሯል፡፡

ይህንን ተከትሎም ሀገራት የሰላም ቦርዱ ቋሚ ኮሚቴ አባል እንዲሆኑ ጥሪ እየቀረበላቸውም ይገኛል፡፡

እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከተደረሰ ወዲህ ሃማስ አርብ እለት ለፈጸመው ጥሰት ቅዳሜ በሰጠችው ምላሽ ቢያንስ 30 ሰዎች መገደላቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here