እናት ባንክ ለጆይ ኦቲዝም ማዕከል ሁለት መቶ ሺህ ብር የበዓል ስጦታ አበረከተ

እናት ባንክ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ለጆይ ኦቲዝም ማዕከል የሁለት መቶ ሺህ ብር የበዓል ስጦታ አበርክቷል።
የባንኩ የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች በኒያ ፋውንዴሽን ተገኝተው፣ ፋውንዴሽኑ እየሰራ የሚገኘውን በጎ ተግባራት ጎብኝተዋል።
ማዕከሉ ከሚንከባከባቸው ኦቲዝምና ተዛማጅ የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸው ሕፃናትና ወጣቶች ጋር ምሳ በመብላት፣ አቅም ላነሳቸው እናቶች የበዓል ስጦታ በማበርከት፣ እንዲሁም ለፋውንዴሽኑ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የትንሳኤ በዓል ዋዜማን አክብረዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ስጦታውን ያበረከቱት የእናት ባንክ ኮርፖሬት ሰርቪስ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ገነት ሀጎስ፣ ኦቲዝምና መሰል የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት መርዳት የሁሉም ማህበረሰብ ግዴታ መሆኑን ጠቅሰው፣ ወደፊትም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እንደሚወጣ ተናግረዋል።
በወ/ሮ ዘሚ የኑስ የተመሠረተው ኒያ ፋውንዴሽን ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ላለፉት 22 ዓመታት በላይ ኦቲዝምና የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ያለባቸውን ሕፃናት፣ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ከተጋረጠባቸው ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ፣ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች የታደገ በአገራችን የመጀመሪያ የኦቲዝም ማዕከል ነው፡፡
እናት ባንክ በወ/ሮ ዘሚ የኑስ ስም – ዘሚ የኑስ ፊጋ ቅርንጫፍ መሰየሙ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe