“እኛ በባዕድ ጠላት አልተገዛንም፤ ላለንበት ድህነትና ኋላቀርነት የምንወቅሰው ሌላ አካል የለም”

በዚህ ጉዳይ ሚሊዮን ሰው ስለጻፈ ምንም ማለት አልፈልግም፤ እኔ ከልጅቷ ጋር ያለኝ ችግር ቅኝ ግዛትን አቅልላ የተመለከተችበት መንገድ ብቻ ነው። ይህንን ኮሜንት ጓደኛዬ ናት አስገርሟት የላከችልኝ።
በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሳምንታት በደቡብ አፍሪካ ምክንያት ስናወራ ነበር። እሷ አውሮፓ ስለምትኖር አንዳንድ አፍሪካውያንን ካየችው፣ እኔም ካስተዋልኩት ተነስተን!
ስለ ደቡብ አፍሪካውያን ካለኝና ከማምንበት መረጃ—ከአንዳንድ አሳማኝ Conspiracy Theories አንጻር—ኔልሰን ማንዴላ እስር ቤት ነው የሞተው፤ ትግላቸውም ተሽጧል።
በአለም ሕዝብ ዘንድ ካገኙት ዝና እና ክብር አንጻር “Scam የሆኑ ሰዎችና ታሪኮች ካሏቸው መካከል የማንዴላ እና የዚያ ሽማግሌ ሕንዳዊ ጋንዲ ታሪክ ይገኝበታል።
በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ሰው ይሞግታል፤ እኔም ለሙግት ጋብዤአችኋለሁ።
ያም ሆነ ይህ፣ ደቡብ አፍሪካውያን የሚኩራሩበትን የተፈጥሮ ሀብታቸውን ዳይመንድን ልክ እንደ ማንኛውም የዓለም ሕዝብ በዜና መልክ ነው የሚያዩት እንጂ ተጠቃሚዎች አይደሉም። ታላቁና ዘመናዊው ከተማቸው ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በገዛ ሀገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ ነው የሚኖሩት።
አስታውሳለሁ፣ ከአመታት በፊት በአንድ KG ትምህርት ቤት ውስጥ የተቀረጸ ቪዲዮ ተለቆ፣ ደቡብ አፍሪካውያንን ሳይሆን ሌሎች አፍሪካውያንን አስቆጥቶ “ትሬንድ” ሆኖ ነበር። ነጭና ጥቁር ልጆች ለየብቻ ጠረጴዛ ተለይቶ ሲበሉ ያሳያል፤ ይህም እዚያ የተለመደ አሰራር ነው።
ደቡብ አፍሪካውያንን ግን በየጊዜው የሚያበሳጫቸው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በነጮች የሚዘወር መሆኑ ወይም በገዛ ሀገራቸው ሁለተኛ ዜጋ መሆናቸው አይደለም። ይልቁኑ እነሱ ሰንፈውና በድራግ ደንዝዘው መስራት ያልቻሉትን፣ ዝቅ ብሎ ያገኘውን ሥራ ሰርቶ በሀገራቸው የሚለወጠው አፍሪካዊ ወንድማቸው ነው። ምክንያታቸው ራሱ ያስቃል!
እኔ በነጭ ደቡብ አፍሪካውያን ማንነት አምናለሁ፤ አሁን ያለው ነጭ ትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ ነው። ችግሬ እኩል መብት አለማግኘታቸው እንጂ በነጭ ደቡብ አፍሪካዊነት አምናለሁ።
የደቡብ አፍሪካውያን ችግራቸው ስደተኛ ሳይሆን፣ ያሉበት የስነ-ልቦና ቀውስ ነው። ያንን ነው መታገል የሚገባቸው፤ ሊጠሉት የሚገባው ስደተኛ ወገናቸውን ሳይሆን፣ በገዛ ሀገራቸው ሁለተኛ ዜግነትን የተቀበለውን ሕሊናቸውን ነው።
ወደ ዋናው ነጥቤ ስመለስ፣ ቅኝ ግዛት ከዝርፊያና ከኢኮኖሚ ብዝበዛ በላይ ትልቅ የስነ-ልቦና ጫና እና ቀውስ ነው የሚፈጥረው። በታሪክ፣ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፣ “ተበድያለሁ” የሚል ማህበረሰብ ትልቅ የማንነትና የስነ-ልቦና ቀውስ ያስተናግዳል። ለትውልድ የሚያወርሰው “Victim Mentality እና የበታችነት ስሜትን ጨምሮ ።
ይህ አብዛኛው በቅኝ ግዛት የተገዛ አፍሪካዊ ወይም በታሪክ “ተበድያለሁ” በሚል ማህበረሰብ ውስጥ የሚከሰት ነው። ብዙ ጊዜ እነዚህ ማህበረሰቦች ለፀብ ዝግጁ ናቸው፤ ሁሉም ነገር ለጥቃት፣ ከጥላቻና ከዘረኝነት የመጣ ይመስላቸዋል። አብዛኛው አፍሪካዊ በአውሮፓ ወይም ነጭ ሕዝብ ባለበት ሀገር ሲኖር የሚያሳየው ምላሽ ተራ አለመግባባትን ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ እነሱን ለማጥቃት የተደረገ ይመስላቸዋል፤ በትንሽ በትልቁ ቱግ ይላሉ፣ አላስፈላጊ ምላሽ ይሰጣሉ፤ ብቻ ብዙ ነገር።
እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ማህበረሰብ እንዲህ አይነት ችግሮች የሉብንም። ይህም ቅኝ ካለመገዛት ያተረፍነው፣ አንዱ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ አለመግባታችን ነው።
ሆኖም ጭቆና ብዙ መንገድ አለው፤ አዎ፣ ጨቋኝ ከውጪ ብቻ አይመጣም። እኛ የማህበረሰብ ሕግ፣ ደንብ፣ ባህልና ወግ ተጨቋኞች ነን። የቆሻሻ አስተዳደርና የፖለቲካ ሥርዓት ተጨቋኞች ነን።
እንደ ሀገር የተሰሩብን አሻጥሮች እንዳሉ ሆነው፣ በቅኝ በተገዙ ሀገራት መከበባችንና ያሳለፍናቸው የውጭ ጦርነቶች ለድህነታችን የራሳቸው አስተዋጽኦ አላቸው። ትልቁ እና ዋናው ግን የሀገር ውስጥ ጦርነታችን ነው። ከደርግ እስከ አሁኑ ጊዜ ድረስ እርስ በርስ የተላለቅንበት የፖለቲካ ሥርዓት ውሳኔዎችና መንግሥቶቻችን—የዚህ ሁሉ ቅኝ ተገዢዎች ነን።
አሁን የኢትዮጵያ ሕዝብ “ነፃ ነኝ” ማለት ይችላል? ግድ ጠላት ከውጪ መምጣት አለበት ወይ? አዎ፣ እኛ በባዕድ ጠላት አልተገዛንም፤ ላለንበት ድህነትና ኋላቀርነት የምንወቅሰው ሌላ አካል የለም። ምክንያቱም ፈቅደንና መርጠን ያለንበት ሕይወት ነው።
በዚህ አዙሪት ነው የምንቀጥለው። ካለፈው መንግሥት የሱፐርማርኬት የዕቃ ዋጋ የአሁኑ ስለሚበልጥ ብቻ፣ ያለፈውን አምባገነን Dictator የምንናፍቅና የምናወድስ ሕዝቦች ነን። ቅኝ ባንገዛም የነፃነትን ዋጋ በደንብ አናውቅም። እንደ ዜጋ ከክልል ክልል መንቀሳቀስ አለመቻላችን፣ በሰላም ወጥቶ መግባት አለመቻላችን፣ የሃሳብ ነፃነት አለመኖሩ፣ ሥራ አጥነትና የዜግነት መብታችንን መነጠቃችን በግፍ የሚያልቀው የሰው ህይወት አይደለም የተሻለ መንግሥት ንፅፅር ውስጥ የሚያስገባን፤ የቁስ ዋጋ እንጂ!
ካሁን በኋላ በሚመጣው ሥርዓትም ቢሆን ኑሮ ስለሚወደድ “ይሄኛው ይሻለናል” ማለታችን አይቀርም።
በእርግጥም፣ ብዙ አይነት ቅኝ መገዛት አለ። (nani Adoniya)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe