በልጅነት ዕድሜ ማንበብ ምን ይጠቅማል?
በእንግሊዝ ከሚገኙት የካምብሪጅ እና የዋርዊክ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቻይና ከሚገኘው የፉዳን ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ተመራማሪዎች ረዘም ላለ ጊዜ ከ10,000 በላይ አሜሪካው ታዳጊዎች ላይ በልጅነት ማንበብ ባለው ጠቀሜታ ላይ ጥናት አከናውነው ነበር፡፡ በጥናቱ ቃለ መጠይቆች፣ ፈተናዎች፣ የአእምሮና የባህሪ ግምገማዎች እንዲሁም የአንጎል ምስል ምርመራን (brain scans) ጨምሮ ሰፊ መረጃዎች ተወስደው ተተንትነዋል፡፡
በጥናቱ ምን ድምዳመሜ ላይ ተደረሰ?
ከሁለት ዓመት በፊት በታዋቂው Psychological Medicine በተሰኘው የሕክምና መጽሔት ላይ በወጣው የጥናት ውጤት መሰረት፣ ከሁለት እስከ ዘጠኝ ዓመታቸው ከመማሪያ መጻሕፍት ባሻገር ለደስታ ሲያነብቡ የነበሩ ልጆች በአዳጊነት እድሜያቸው የተሻለ የትምህርት ውጤት እንዳስመዘገቡ፣ የማስታወስ አቅማቸውም ከፍ ያለ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
በተጨማሪም እነዚህ በልጅነታቸው ለደስታ ሲያነብቡ የነበሩ ልጆች፣ የተሻለ የአእምሮ ደህንነት እንዳላቸው በጥናቱ ታይቷል። በእነዚህ ልጆች ላይ የጭንቀትና የድብርት ምልክቶች አነስተኛ ሆነው ተገኝተዋል። እንዲሁም የተሻለ ትኩረት የመስጠት ብቃት እንዳዳበሩ፣ እንደ ጠብ አጫሪነትና ህግ መጣስ ያሉ የባህሪ ችግሮችም ብዙ እንደማይስተዋልባቸው በጥናቱ ታይቷል፡፡
ይህ የኪን መልዕክት ነው
ይህ በታዋቂ የጥናት ባለሙያዎች በበርካታ ልጆች ላይ የተሰራው ጥናት ለእርስዎ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው እናምናለን፡፡ ኪን የልጆች መጻሕፍት እንድትመጣ ያደረጓትም ይህን መሰል የጥናት ውጤቶች ናቸው፡፡
በኪን የልጆች መጻሕፍት፣ መጻሕፍትን ከማቅረብ በላይ ልጅዎን በጥቂት እገዛ ልጅነቱን የተሻለ እንዲያደርጉ ስለምናግዞት ደስተኞች ነን፡፡ የተሻለ ቤተሰብ፣ የተሻለ ለጅነትን ይፈጥራልና፡፡
ከ2 እስከ 9 ዓመታቸው ከመማሪያ መጻሕፍት ባሻገር የሚያነቡ ልጆች የተሻለ የትምህርት ውጤትና የማስታወስ አቅማቸውም ከፍ ያለ እንደሆነ ተገለጸ
Sourceኪን ኢትዮጵያ

