“ከትዳር በላይ” የተሰኝ ኮሜዲ ቴያትር እሁድ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በ12 :00 ሰዓት በአለም ሲኒማ በድምቀት ይመረቃል።
“ከትዳር በላይ” የተሰኝ ኮሜዲ ቴያትር እሁድ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም በ12 :00 ሰዓት በአለም ሲኒማ በድምቀት እንደሚመረቅ የትያትሩ አዘጋጆች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በተለያዩ የመድረክ፣ የፊልም እና የቴሌቭዥን ምርጥ ሥራዎቿ የምትታወቀው ተዋናይት መስከረም አበራ ፕሮዲውስ ያደረገችው እና በደራሲ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተጽፎ በዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ የተዘጋጀው “ከትዳር በላይ” የተሰኘው ኮሜዲ ቴያትር ዝነኞቹ ተዋንያን ሽዋፈራው ደሳለኝ ፣መስከረም አበራ ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መዓዛ ገ/ሕይወት ፣ የማታወርቅ ታደሰ ተሳትፈውበታል
በመግለጫው እንደተገለጸው ከትዳር በላይ ኮሜዲ ቴያትር ከ10 አመት በፊት በመድረክ እንደታየ የተገለፀ ሲሆን አሁን በአዲስ መልክና በተሻለ መልኩ መሰራቱ ተነግሯል
በተጨማሪም የትያትሩ ፅሁፍ በተደጋጋሚ ታርሞ የተፃፈና 3ወር ልምምድ እንደተደረገም ተገልጿል።
ከትዳር በላይ ኮሜዲ ቴያትር የኮሜዲ ዘውግ ያለው ሲሆን ሳቅ የሚያስጭር ብቻ ሳይሆን ቁምነገርም የሚጨበጥበት እንደሆነ ተነግሯል።
የትያትሩ መግቢያ 1000 ብር ሲሆን ይህ ዋጋ ግን ለምርቃቱ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።
በተጨማሪም ትያትሩ ሚያዚያ ላይ እስራኤል ሀገር እንደሚታይ ተነግሯል።
(በድሬቲዩብ ሪፖርተር)
“ከትዳር በላይ” ኮሜዲ ቴያትር በእስራኤል እንደሚታይ ተገነረ

