ከነገ ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ተጓዦች የቪዛ ዋስትና እስከ 15ሺ ዶላር ገንዘብ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል

ከነገ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ተጓዦች የቪዛ ዋስትና ገንዘብ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የቪዛ ዋስትና ገንዘብ ከሚጠየቁ ሀገራት ወስጥ መካተቷን ያስታወሰው ኤምባሲው ለንግድ ወይም ለጉብኘት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ብቁ ሆነው የተገኙ የቪዛ አመልካቾች ቪዛው ከመሰጠቱ በፊት እስከ 15ሺ ዶላር በዋስትና እንዲያስይዙ እንደሚገደዱም ጠቅሷል፡፡

ሆኖም ተጓዦች የቪዛውን ህግና ደንቦች በሙሉ አክብረው ከተገኙና የተፈቀደላቸው የቆይታ ጊዜ ሳያበቃ ከአሜሪካ ከተመለሱ ያስያዙት የገንዘብ ዋስትና ተመላሽ እንደሚሆን ኤምባሲው ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe