በዓለም ላይ ሃያል ከሆነችው ኢራን ጋር ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የሚደፍር ምንም ዓይነት ጠላት እንደሌለ ቴህራን ገለጸች፡፡
ከ1979 አብዮት አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ኢራን ማንኛውም ጠላት ሀገሪቱን ሊጋፈጣት እንደማይችል አረጋግጣለች ሲሉ የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር ጀነራል መናገራቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ሃያሏን ኢራንን ሊጋፈጥ የሚችል ምንም ምድራዊ ሃይል የለም በማለት ነው ጀነራሉ የተናገሩት፡፡
የኢራን ጦር ጀነራል እስላማዊ ሪፐብሊኳን ሀያሏን ሀገር ችሎ ሊጋፈጥ የሚችል ጠላት በመላው ዓለም የለም ብለዋል፡፡
የሀገሪቱ ምድር ጦር ጀነራል አሊ በዓለም ላይ እኛን ሊገዳደር የሚችል አቅም ያለው ጠላት የለም ብለዋል፡፡ ጀነራሉ አክለውም ከ1979 አብዮቱ አንስቶ እስካሁኗ ስዓት ድረስ ከኢራን ጋር መጋፈጥ የሚችል ጠላት አለመኖሩን መግለጽ እወዳለሁ ብለዋል፡፡
ጦር ጀነራሉ በዚህ ወቅት ዩናይትድስ ስቴትስ እና እስራኤል እያጋጠማቸው ያለውን ውርደት መላው ዓለም እየተመለከተ ነው፤አዲስ ጥቃት ለመሰንዘር ፍላጎቱ ካላቸውም በእኛ በኩል ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ዝግጅት ጨርሰናል በማለት ገልጸዋል፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብም አሜሪካ እና እስራኤል አዲስ ጥቃት የሚሰነዝሩ ከሆነ እጅግ አጥፊ የሚባል አጸፋ እንደሚሰጥና ጦርነቱም ወደ ጠቀናው የሚሰፋ እንደሚሆን በመግለጽ እያስጠነቀቀ ነው፡፡
ሃያሏ ኢራን በጅግናው ህዝብ አንድነት እና ትብብር ሁልጊዜም ከፍ ትላለች ያሉት አዛዡ፤ጠላት በእኛ ላይ የነደፈውን እኩይ አላማ ማሳካት ያልቻለው በቆራጥነታችን ነው ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ጦር የድርድር ውጤቱን ሊያስቀለብስ የሚችል ጥቃት በኢራን ላይ ፈጸመ፡፡
አሜሪካ ይህንን ጥቃት ያደረሰችው ከኢራን ጋር በቀናት ውስጥ ስምምነት ላይ እንደሚደረስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል በምትገልጽበት በዚህ ስዓት ነው፡፡ በርግጥ ይህ የአሜሪካ አዲስ ጥቃት በሂደት ላይ ያለውን ድርድር በምን መልኩ ሊጎዳው እንደሚችል ግልጽ አለመሆኑም ተያይዞ እየተነሳ ነው፡፡
አሜሪካ ይህንን የምትለው ጥቃቱ ራስን የመከላከል ነው በሚል ስሌት ነው፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ አሜሪካ አዲስ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ ቀጠናውን በሙሉ ሊያተራምስ የሚችል የአጸፋ ጥቃት እንደሚፈጽም በተደጋጋሚ እየገለጸ ባለበት ወቅት ነው ይህ ጥቃት የተፈተመው፡፡
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ጀልባዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ኢራናዊያን መገደላቸው ታውቋል፡፡
ይህ ጥቃት በዋነኝነት ኢላማ ያደረገው በሚሳኤል ማከመቻዎች እና ፈንጂ ጣይ ጀልባዎች ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡ የአሜሪካ ጦር ጥቃቱ ራስን መከላከል እንደሆነ አስታውቋል፡፡
የሀገራቱ የጦር አውሮፕላኖች በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በደቡባዊ የላራክ ደሴት ባደረሱት ጥቃት በርካታ የኢራን ዜግነት ያላቸው ሰዎች መገደላቸውን ታስኒም የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
ምንም እንኳን የዜና ወኪሉ የሟቾቹን ብዛት ይህ ነው ብሎ በቁጥር ባይገልጽም፤አንዳንዶች ግን አራት መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
ይህ ዜና የተሰማው ዋሽንግተን እና ቴህራን ሦስት ወራት ያስቆጠረውንና በቀጠናውም ሆነ በመላው ዓለም ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለውን ጦርነት በዘላዊ ስምምነት ለማጠናቀቅ ጥረት እያደረጉ ባሉበት በዚህ ስዓት ነው፡፡
በዚህ ስዓት በሁለቱም ወገኖች በኩል ወደ ስምምነት ለመድረስ መልካም የሚባል ሂደት ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
ሁለቱን አገራት ወደ ዘላቂ ስምምነት እንዳይደርሱ ካደረጋቸው ነጥቦች መካከል ወደ ጦር መሳሪያነት ለመለወጥ ተቃርቧል የተባለው የዩራኒየም ጉዳይ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህ በከፍተኛ ደረጃ የበለጸገው ዩራኒየም ወይ ለእኛ ተላልፎ መሰጠት ይኖርበታል፤አልያ ደግሞ እኛ እየተመለከትነው ወደሆነ ቦታ ተወስዶ መወገድ አለበት ብለዋል፡፡
ትላንት ሰኞ እለት የፓኪስታኑ ፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ያለው ድርድር ወደ ስምምነት መቃረቡን ለቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደገለጹላቸው የቻይና መገናኛ ብዙሃን ጽፈዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል አሲም ከቴህራን ሰዎች ጋር ከተመካከሩ በኋላ ወደ ቤጂንግ አቅንተው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ፓኪስታን ሀገራቱን በማሸማገል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች፡፡ አሁን በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል ያለው ሁኔታ ወይ ብዙዎች ተስፋ እንጣሉበት ከስምምነት ላይ ይደርሳል አልያ ደግሞ ውጭ ጉዳይ ማርክ ሩቢዮ እንደተናገሩት ከስምምነት መድረስ ካቃተን ጉዳዩ በሌላ መንገድ ይያዛል እንዳሉት አዲስ ጥቃት ሊከፈት ይችላል፡፡//

