ከእስራኤል ወደ ኦስትሪያ እየበረረ የነበረ አውሮፕላን በድንገት እንዲያርፍ ተደረገ

ከእስራኤል ወደ ኦስትሪያ እየበረረ የነበረ አውሮፕላን የቦምብ ጥቃት ሊኖር ይችላል በሚል በድንገት እንዲያርፍ ተደረገ።
ከእስራኤል ወደ ኦስትሪያ እየበረረ የነበረ የኦስትሪያ አየር መንገድ አውሮፕላን የቦምብ ጥቃት ሊኖር እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ከደረሰው በኋላ በድንገት ቡልጋሪያ ለማረፍ ተገደደ።
የቡልጋሪያ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የኤርባስ ኤ320 አውሮፕላን እሁድ ምሽት ከቴል አቪቭ ወደ ቪየና እየተጓዘ ሳለ በዋና ከተማዋ ሶፊያ በድንገት እንዲያርፍ እና ተሳፋሪዎቹ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርጓል ብሏል።
የቡልጋሪያ አየር ኃይል አውሮፕላኑን ለማጀብ ሚግ-29 የተዋጊ አውሮፕላን ተጠቅሟል ሲል የትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጨምሮ ገልጿል። በአውሮፕላኑም ሆነ በመንገደኞች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን ጠቅሰው ምርመራም እንደተጀመረ አስታውቀዋል።
ባለፈው ወር አንድ ረዳት አብራሪ ወደ ቴል አቪቭ ሲጓዝ የነበረውን የፍላይዱባይ አውሮፕላን ካፒቴን ላይ ጥቃት ፈጽሟል።
የቡልጋሪያና የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን የቦምብ ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረ ዘግበዋል። የኦስትሪያ አየር መንገድ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ሳይሰጥ ስጋት መፈጠሩን አረጋግጧል። አንድ ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት በአውሮፕላኑ ውስጥ 51 ተሳፋሪዎች እና ስድስት የበረራ አባላት ነበሩ።
ባለሥልጣናት አውሮፕላኑ ሶፊያ ውስጥ ካረፈ በኋላ የደኅንነት ፍተሻ አካሂደዋል።
የበረራ ክትትል መረጃዎች እንደሚያሳዩት የኦስትሪያ አየር መንገድ አውሮፕላን እሁድ ምሽት ከቴል አቪቭ ቤን ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ከወጣ ከሦስት ሰዓታት በኋላ ሶፊያ በሚገኘው ቫሲል ሌቭስኪ አውሮፕላን ማረፊያ አርፏል።
ባለፈው ሳምንት ክሮሺያ እና ጀርመን ከግሪክ ደሴት ኮርፉ ወደ ጀርመን ኑረምበርግ ከተማ እየበረረ የነበረ አውሮፕላን ላይ በስህተት የጠለፋ ማስጠንቀቂያ ከተላከ በኋላ የጦር አውሮፕላኖቻቸውን አሰማርተው ነበር።
ቢቢሲ የኦስትሪያ አየር መንገድ ባለቤት የሆነውን ሉፍታንዛን ተጨማሪ አስተያየት ጠይቋል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe