ከድንጋይ ወፍጮ እስከ ዓለም አቀፍ ገበያ የወ/ሮ ሔዋን አስደናቂ የስኬት ጉዞ!
በልጅነቷ እናቷ በድንጋይ ወፍጮ ቅመማ ቅመም ሲፈጩ ተመልክታ ያደገችው ወ/ሮ ሔዋን ቀለመወርቅ፣ ያንን የቤት ውስጥ ሥራ በ730 ሚሊዮን ብር ካፒታል በደብረ ብርሃን ከተማ ወደተመሠረተው “ሔዋን ስፓይስ ማኑፋክቸሪንግ” ፋብሪካ አሳደገችው። ፋብሪካው በርበሬን፣ ሚጥሚጣን እና ሽሮን ጨምሮ ከ30 በላይ የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ቅመማ ቅመሞችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማቀነባበር በሰዓት እስከ 2 ቶን የማምረት አቅም በማሳየት ላይ ይገኛል።
የወ/ሮ ሔዋን አስደናቂ የስኬት ጉዞ!
ይህ ትልቅ የኢንዱስትሪ ተቋም የቤተሰብ ልምድን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር የኢትዮጵያን ቅመማ ቅመም በጥራትና በደረጃ ለገበያ እንዲቀርብ አድርጓል። የፋብሪካው ዕቅድ በሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ ሳይወሰን ምርቶቹን ዱባይ፣ ቶሮንቶ፣ ለንደን፣ ኒውዮርክ እና በአማዞን (Amazon) መድረኮች ጭምር ለዓለም አቀፍ ሸማቾች በማድረስ የአገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
የወ/ሮ ሔዋን ታሪክ ባህላዊ ሥራ በራዕይ፣ በትጋት እና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሲታገዝ እስከ ዓለም አቀፍ ገበያ ሊዘልቅ የሚችል ትልቅ የኢንዱስትሪ ዕድገት ማምጣት እንደሚችል ህያው ማሳያ ነው። ከእናቷ እጅ የተጀመረው ይህ አርአያነት ያለው የንግድ ጉዞ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍ ከፍ የሚያደርግ አስደናቂ ምዕራፍ ሆኗል።
ከድንጋይ ወፍጮ እስከ ዓለም አቀፍ ገበያ የወ/ሮ ሔዋን አስደናቂ የስኬት ጉዞ!
SourceAddis maleda

