ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን አርቲስት ይገረም ደጀኔን የብራንድ አምባሳደር አድርጏ ሾመ

ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን በዛሬው እለት አርቲስት ይገረም ደጀኔን የብራንድ አምባሳደር አድርጏ መሾሙን አስታውቋል።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው የአምባሳደርነት ፊርማው አርቲስት ይገረም ደጀኔ በኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ለቴሌቪዥን፤ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያዎች መስራትን ያጠቃልላል፡፡
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን ከአርቲስት ይገረም ደጀኔ ጋር የተለያዩ ማህበራዊ ግዴታዎቻችንን ለመወጣት እና ህዝቡ ጋር የነበረውን ተደራሽነት በተሻለ መልኩ ለማጎልበት የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ስምምነቱን እንዳረገ ተነግሯል።
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን “Economies of Scale” ላይ የተመሰረተ ሞዴል ቀርዖ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰባችንን ክፍሎች የቤት ባለቤት እያደረገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን
ወደ ገበያው ከተቀላቀለ በአንድ አመት ከስድስት ወር ውስጥ መቶዎችን በአዲስ አበባ ስድስት ሳይቶች እና በባህርዳር ከተማ የቤት ባለቤት አድርጓል ተብሏል።
በመርሀገብሩ ላይ እንደተገለጸው ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን እስካሁን ድረስ 2 ጊዜ የእጣ ማውጣት ስነስርአት አከናውኗል ።
በአሁኑ ሰዓትም 20,000 የሚደርሱ አባላት እንዳለው ገልጾ ኪ መንደር የተሰኘ የመኖሪያ መንደር ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe