ኪም ጆንግ ኡን የዓለምን ስጋት የቀሰቀሰ አዲስ ዛቻ አሰሙ

ኪም ጆንግ ኡን የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያድግ አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በአንድ አዲስ የኒውክሌር ቁስ ማምረቻ ተቋም ላይ ባደረጉት ድንገተኛ ጉብኝት ወቅት ነው፡፡
ፒዮንግያንግ የሀገሪቱን የኒውክሌር ጦር ሃይል በከፍተኛ ፍጥነት ለማጠናከር የታለመ ታላቅ የወደፊት ዕቅድ ማጽደቋን አረጋግጣለች፡፡
ፕሬዝዳንት ኪም ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ለጦር መሳሪያ የሚሆን የኒውክሌር ቁስ ምርት ከእጥፍ በላይ ማደጉን ገልጸዋል፡፡ የሀገሪቱ የወታደራዊ ኒውክሌር አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያድግ ቃል ገብተዋል፡፡
ፒዮንግያንግ ከአሜሪካና ከምዕራባዊያን የሚሰነዘርባትን ማዕቀብና ጫና ወደ ጉን በመተው የጀመረችው የኒውክሌር ጉዞ የማይቀለበስ እና በህገ-መንግስቷ የጸደቀ መሆኑን በይፋ አስታውቃለች፡፡
የሀገሪቱ የዜና ወኪል ዛሬ እንደዘገበው ኪም በአንድ የኒውክሌር ቁስ ማምረቻ ተቋም ባደረጉት ጉብኝት ወቅት የኒውክሌር ሃይል በከፍተኛ ፍጥነት ለማጠናከር ዕቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ክምችቷ በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካ የጦር ሃይሎች ሊሰነዘርባት ከሚችል ጥቃተ ራሷን መከላከያ አድርጋ ትመለከተዋለች፡፡
ሰሜን ኮሪያ ለአሁኑ የኒውክሌር መታጠቅ ደረጃ ለመብቃት ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ሚስጥራዊና ግልጽ ጉዞ ማድረጓ ይታመናል፡፡
ሰሜን ኮሪያ እ.ኤ.አ በ1993 የኒውክሌር መሳሪያዎችን ላለማስፋፋት ከሚደነግገው ዓለም አቀፍ ስምምነት ራሷን ማግለሏ ይታወሳል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe