ክብር እና ኃላፊነት በጃፓን!

ጃፓን ውስጥ አንድ በጣም አስደናቂ እውነተኛ ታሪክ አለ፡፡
አንድ ባቡር ጣቢያ ለአንዲት ተማሪ ሲል ለዓመታት በኪሳራ ሲሰራ ኖሯል፡፡
ካሚ ሺራታኪ ባቡር ጣቢያ ነው፡፡ በጃፓን ሆካይዶ በተሰኘች ከተማ ይገኛል፡፡ ይህ ባቡር ጣቢያ የተሳፋሪ ቁጥር በጣም ሲያሽቆለቁልበትና የሚጠቀመው ሰው ሲያጣ ከሚከስር ይዘጋ የሚል ሃሳብ ቀረበ፡፡ የባቡር ጣቢያው ሃላፊዎች ጥናት ሲያደርጉ አንዲት ተማሪ ብቻ ወደትምህርት ቤቷ ለመሄድና ለመመለስ በየቀኑ ይህንን ባቡር ጣቢያ እንደምትጠቀም ታወቀ፡፡
ባለስልጣናቱ ጣቢያውን ከመዝጋት ይልቅ አንድ አስደናቂ ውሳኔ አሳለፉ፡፡ ጣቢያው ልጅቷ ትምህርቷን እስክታጠናቅቅ ድረስ ስራውን እንዲቀጥል ወሰኑ፡፡ ለብዙ ዓመታት ባቡሩ ሳይዛነፍ በሰዓቱ እየመጣ ወደትምህርት ቤት የምትሄደውን ልጅ ማሳፈርና ከትምህርት ቤቷ ስትመለስ በሰዓቱ እየደረሰ ወደቤቷ የመመለስ አገልግሎቱን መስጠት ቀጠለ፡፡ ልጅቷ ትምህርት መጨረሷ ሲረጋገጥ ባቡር ጣቢያው እስከወዲያኛው ተዘጋ፡፡
ይህ ድርጊት አሁን ድረስ በዓለም ላይ የኃላፊነት ምሳሌ እና ለትምህርት የተደረገ ክብር መግለጫ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡
በጣም ስትሰለጥን እንዲህ ነው የምታስበው!

(መላኩ ብርሃኑ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe