ኮስሞፖሊታን ሪል ስቴት፣ በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በቤቶች ግንባታ እና በሌሎች ዘርፎችም ላይ ተሠማርቶ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ጥቅምት 3 2016 ቤቶቹን ለገዢዎች አስተላልፏል። የቤቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓትም ተካሂዷል ።ድርጅቱ፣ በይፋ ከተመሠረተ 5 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ዓመታት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩ ባሻገርም የመኖሪያ ቤት ችግርንም ለማቃለል የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ።
ኮስሞፖሊታን የስሙ ትርጉም በአንድ ቦታ ተሰባስቦ የሚኖር የከተማ ማህበረሰብን የሚያመለክት ነው። ድርጅቱ እንደ ስሙ የከተማን ኑሮ ምቹ ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ አስበልጦ እየሠራ ይገኛል ።በቦሌ ጃፓን ኤምባሲ አቅራቢያ ሠርቶ ያጠናቀቀው ጂ +11 የሆነ በ 700 ካሬሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ባለ ምቾት አፓርታማ የቤት ገዢዎችን ፍላጎት ያሟላ እንደሆነ ታውቋል።
የስፖርት ማዘውተሪያ ጂም፣ሳዋናና ስቲም የተሟላላቸው የኮስሞፖሊታን መኖሪያ ቤቶች የ24 ሰዓት ኤሌክትሪክ የተመቻቸላቸው ሲሆን አጠቃላይ በዕለቱ ቤቶች ለነዋሪው ይተላለፋሉ ።የኮስሞፖሊተን መኖሪያ ቤቶች በሙያው የላቀ ልምድ ባካበቱ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሙያዎች የተገነቡ ሲሆን የቤቶቹ የአሠራር ጥራትም ደረጃውን የጠበቀ ነው። በዋጋም በተመጣጣኝ የቀረቡ ናቸው።
ድርጅቱ፣ ይህን የግንባታ ስራ ሲያከናውን ለ250 ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል ።ኮስሞፖሊታን፣ በአሁኑ ሰዓት ኦሎምፒያ ጂ+17 ህንጻ እንዲሁም በፒያሳ ኤሊያና ሞል አካባቢ ለሱቅና ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የገበያ ማዕከል ግንባታ የሚጀምር ሲሆን ይህም ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ ዕድል ይፈጥራል ።
በአስመጪና ላኪነት ፣በቤት እና ቢሮ እቃዎች ፣በወረቀት ማምረት እንዲሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የተሠማራው ኮስሞፖሊታን ለደንበኞቹ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ቀዳሚ ግቡ ነው።
፣ኮስሞፖሊተን በቅርቡ ሠርቶ ያጠናቀቃቸውን ቤቶች ለማስረከብ ልዩ የምረቃ መርሐ -ግብር ያዘጋጀ ሲሆን በዚህ ምረቃ ላይ ልዩ የክብር እንግዶች ታድመዋል።
ሀሴት የሙዚቃ ቡድን አባላትም በመርሀ-ግብሩ ላይ ታድመው በመገኘት ለፕሮግራሙ ድምቀት ሰጥተዋል ።
የድርጅቱ የማርኬቲንግ እና ሽያጭ ሥራ መሪ ሜላት ጥላሁን ለሚድያ ሰዎች በሰጡት መግለጫ የኮስሞፖሊታን ቤቶች ልዩ የሚያደርጋቸው አጨራረስ ላይ በጥሩ ሁኔታ የተጠናቀቁ መሆናቸው ነው ማለታቸውን የመርሀ-ግብሩ አዘጋጅ እና የሚድያ ፣የህዝብ ግንኙነት ሥራውን ያከናውነው ተወዳጅ ሚድያ እና ኮሚኒኬሽን ለዝግጅት ከፍላችን ከላከው ጋዜጣዊ መግለጫ ተረድተናል ።

