ወጣቶች ”ቶች ”ተማሩ፣ ሰልጥኑ፣ ውደዱ፣ ተወደዱ፣ ዝሙትን ሽሹ”

1. የወሲብ ስሜታችሁን መቆጣጠራችሁ የስኬታችሁ ወይም የውድቀታችሁ ምክንያት ይሆናል።
2. ፖርኖግራፊና ግለ ወሲብ የስኬት ትልቁ ጠላቶች ናቸው፡፡ አእምሯችሁን ያኮስሳሉ፣ ያጠፋሉ።
3. ልክ ግመል ውሃ እንደሚጠጣው አልኮል ከመጠጣት ተቆጠቡ፡፡ ህሊናችሁን ስታችሁ ሞኞች ከመሆን የከፋ ነገርየለም።
4. ደረጃችሁን ከፍ አድርጉ፤ ዝም ብሎ ስለተገኘ ብቻ ዝቅ ባለ ነገር አትርኩ፡፡
5. ከእናንተ የበለጠ ብልህ ሰው ካገኛችሁ፣ ከእነሱ ጋር ስሩ እንጂ ሩሳችሁን አታወዳደሩ።
6. ችግሮቻችሁን ሊፈታላችሁ የሚመጣ ማንም የለም፡፡ የህይወታችሁ 100% የራሳችሁ ኃላፊነት ነው፡፡
7. በህይወት መድረስ ከምትፈልጉበት ደረጃ ካልደረሱ ሰዎች ምክር አትቀበሉ። ከፍላጎታችሁና ከአላማችሁ ጋር የሚሄድ አስተማሪ ገፆችን መርጣችሁ ተከተሉ።
8. የገንዘብ፣ የጊዜ እና የእምነት ነፃነታችሁ ጠብቁ።ገንዘብ የምታገኙበት አዳዲስ መንገዶችን ፈልጉ። ገንዘብ ስሩ፤ በሚያሾፉባችሁና በሚቀልዱባችሁ ፌዘኞች ጊዜ አታጥፉ/ችላ በሏቸው፡፡
9. ለመለወጥ ብዙ መፅሀፍ ማንበብ ወይም መርጃ መጻሕፍት ማገላበጥ አያስፈልጓችሁም፤ የሚያስፈልጋችሁ ተግባርና ራስን መገዛት ብቻ ነው። ራሳችሁን ግዙ!
10. አደንዛዥ እጾችን አስወግዱ። በተለይ እንደ ጫትና ሀሺሽ፣ አልኮል መጠጥና ሲጋራ ያሉትን አስወግዱ።
11. በኔትፍሊክስ የማይረባ ይዘት እየተመለከታችሁ ጊዜያችሁን ከምታጠፉ፣ ከዩቲዩብ ክህሎቶችን ተማሩ፣ ከGoogle scientifical research አንብቡ።
12.ማንም ስለእናንተ ግድ የለውም። ስለዚህ ዓይን አፋር መሆናችሁን አቁሙና ወጥታችሁ እድሎቻችሁን ፍጠሩ።
13. ምቾት ከሁሉ የከፋ ሱስና ወደ ድብርት/ጭንቀት የሚወስድ ርካሽ ትኬት ነውና አምልጡ።
14. ለቤተሰባችሁ ቅድሚያ ስጡ። መጥፎ ቢሆኑም ወይም ሞኞች ቢሆኑም እንኳ ተከላከሉላቸው፤ ነውራቸውን ሸፍኑ፣ ታዘዙ፣ ተንከባለቡ፣ አክብሯቸውም!
15. አዳዲስ እድሎችን ፈልጉ፤ ከእናንተ የቀደሙ ሰዎችን ተሞክሮ በመውሰድ ተማሩ።
16. መታመናችሁን ቀጥሉበት ሰውን ማመናችሁን ግን አስቡበት፣ ማንንም አትመኑ። አንድም ሰው ቢሆን፣ ምንም ያህል ብትፈተኑ እንኳ። በራሳችሁ እመኑ።
17. ተአምራትን አትጠብቁ፤ እንዲፈጠሩ አድርጉ። አዎ፣ ሁልጊዜ ብቻችሁን ላታደርጉት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን የሰዎችን አስተያየት አትስሙ።
18. ጠንክሮ መሥራትና ጽናት ማንኛውንም ነገር እንድታሳኩ ያስችሏችኋል። ራስን ዝቅ ማድረግ ከፍ ያደርጋችኋል።
19. ራሳችሁን እስክታገኙ/እስክታውቁ ድረስ መጠበቅ አቁሙ። ይልቁንስ ራሳችሁን ፍጠሩ።
20. ዓለም ለእናንተ ስትል ፍጥነቷን አትቀንስም/አትዘገይምና አታማሩ። በምትችሉትና በአቅማችሁ ተንቀሳቀሱ።
21. ማንም ሰው ስለ እናንተ ምንም ዕዳ የለበትም። ለራሳችሁ ራሳችሁን ተጠያቂ አድርጉ።
22. ህይወት የአንድ ተጫዋች ጨዋታ ናት። ብቻችሁን ትወለዳላችሁ፤ ብቻችሁን ትሞታላችሁ። ሁሉም ትርጓሜዎቻችሁ የራሳችሁ ብቻ ናቸው፡፡ በሶስት ትውልድ ውስጥ ትረሳላችሁ ማንምም ለእናንተ ግድ አይሰጠውም። ከመምጣታችሁ በፊትም ማንም ግድ አልሰጠውም ነበር። ሁሉም ነገር የአንድ ተጫዋች ነው፡፡
23. የህይወታችሁ መንገድ ሁልጊዜ ጥገኛ፣ የተጨነቃችሁና ደካማ እንድትሆኑ በሚያደርግ መልኩ የተነደፈ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን መውጫው አንድ ብቻ ነው፤ እሱም ለመውጣት መወሰን። ከራሳችሁ በቀር ማንም እናንተንም ሆነ የምትወዷቸውን ሰዎች አያድንም።
24. ሁሉም ሰው እንደናንተ አይነት ልብ የለውም። ሁሉም ሰው እናንተ ለነሱ ቅን እንደሆናችሁት ለእናንተ ቅን አይሆንም። ለጥቅማቸው የሚጠቀሙባችሁና ያ የህይወታቸው ምዕራፍ ሲያልፍና ፍላጎታቸው ሲሟላ የሚጥሏችሁ ሰዎች ያጋጥሟችኋል። ንቁ ሁኑ!
25. በወጣትነት ዘመናችሁ የሚከተሉትን ለማድረግ ብልሆች መሆን አለባችሁ፦
👉 የሌሎችን ስኬት አክብሩ፣ ቅናትንና ምቀኝነትን አስወግዱ፣ ክፍት አእምሮ ይኑራችሁ፣ ግምቶችን አስወግዱ፣ በዓላማ ተንቀሳቀሱ፣ ምስጋናን ተለማመዱ፣ በታማኝነት ተናገሩ፣ በየቀኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ፣ ከሐሜት ራቁ፣ ንጹህ ምግብ ተመገቡ፣ ይቅርበሉ፣ አዳምጡ፣ ተማሩ፣ ሰልጥኑ፣ ውደዱ፣ ተወደዱ፣ ዝሙትን ሽሹ፣ ሀጢያትን ተጠየፉ፣ ከሱስ ራቁ!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe