ዋሽንግተን እና ቴህራን ከስምምነት ላይ ቢደርሱም ከሊባኖስ ጦሬ አይወጣም ስትል እስራኤል ገለጸች

ቴህራን ከዚህ በኋላ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመው የትኛውም ጥቃት ከአሜሪካ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ ነው በማለት እያስጠነቀቀች ነው፡፡

በስምምነትም ይሁን ያለ ስምምነት ኢራን መቼም ቢሆን የኒውክሌር መሳሪያ ሊኖራት አይችልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔትንያሁ ተናግረዋል፡፡ እኔ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ላይ እስካለሁ ድረስ ደግሞ ይህ ሊሆን የማይችል ነው ብለዋል፡፡ ከወዳጃችን አሜሪካ ጋር ሆነን የኢራንን የኒውክሌር ሳይንቲስቶቿን ማስወገድ ችለናል፤የኒውክሌር ፋክተሪዎቿንም እንዲሁ ማውደም ተችሏል ብለዋል፡፡

ኢራን በትሪሊዮን የሚቆጠር ወጪ የሚያስወጣትን መሠረተ ልማቶችን እንድታጣ አድርገናል፤መልሳ ለመግንባትም አስርት ዓመታትን ይፈጅባታል ብለዋል፡፡ ነገር ግን ከሁሉም ይበልጥ አሳክተናል የምንለው ግን እስራኤልን ከኢራን የኒውክሌር ስጋት መታደጋችን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መንገድ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ እንዲሁም ከአሜሪካ ጦር ጋር ሆነን ባንታገል ኖሮ፤ኢራን አቶሚክ ቦምብ በእጇ ይገባ ነበር ብለዋል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ሁላችንም በሞት አፋፍ ላይ ነበር የምንሆነው ሲሉ አንስተዋል፡፡ እናም አሁን ያደረግነው ይህን ሞት ከእኛ ማራቅ ነው ይህንን ማሳካት ችለናል በማለት በዚህ ጦርነት የተገኘውን ድል አብራርተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ኋላ መለስ ብለውም ማንም ባልጠበቀው ሁኔታ ሁሉም ታጋቾቻንን ከጋዛ ማስመለስ ችለናል በማለት በጋዛ የነበረውን ተጋድሎ አብራርተዋል፡፡

ነገር ግን ይህንን ማድረግ እንደምችል ብዙዎች ተጠራጥረውን ነበር፤እንዲያውም አንዳንዶች ተሸንፈን እንድንተውና ወደ ራፋም እንዳንገባ ጠይቀውን ነበር፤እኔ ግን ያን መቀበል አልቻልኩም በመጨረሻ ግን ሁላችሁም እንደምታውቁት አሳክተነዋል ብለዋል፡፡

አሁን አንድ ነገር በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ነገር ቢኖር፤ኢራን በጣም በከፋ የኢኮኖሚ ጫና ውስጥ ነው የምትገኘው፤አገዛዙም መሰንጣጠቅ ገጥሞታል መቼ ያበቃለታል የሚለውን መናገር ባይቻልም መውደቁ ግን አይቀርም ብለዋል፡፡ በኢራን ያለው አገዛዝ መውደቅ እንደሚችል ለኢራናዊያንን ምቹ ሁኔታን ፈጥረናል ብለዋል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe