የ18 ዓመቱ ሕንዳዊ የዓለም ትንሹ የቼዝ ሻምፒዮን ሆነ

የ18 ዓመቱ ሕንዳዊ ጉኬሽ ዶማራጁ በሲንጋፖር በተካሄደ የቼዝ ጨዋታ የቻይናውን ዲንግ ሊረን በማሸነፍ ትንሹ የዓለም የቼዝ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።
ስካሁን በዚህ የእድሜ ደረጃ የዓለም የቼዝ ሻምፒዮን መሆን የቻለ የለም የተባለ ሲሆን፣ የ18 ዓመቱ ሕንዳዊ 1.96 ሚሊዮን ዶላር እና “ታዳጊ የቼዝ ኮከብ” የሚል ማዕረግ ተሰጥቶታል።
ባለፉት ሁለት ኦሊምፒያዶች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈው ጉሽኬ፤ እ.ኤ.አ. በ2022 ለሕንድ በቡድን የነሐስ እና በ2024 በቡዳፔስት የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።
እነዚህ ውጤቶቹ ታዲያ የአምናውን ሻምፒዮን ቻይናዊውን ዲንግ ሊረንን ለመወዳደር እንዳስቻለው ነው የተገለጸው።
አምስት ጊዜ የዓለም የቼዝ ሻምፒዮን በሆነው ቪስዋናታን አናንድ የሚሰለጥነው ጉሽኬ ከ10 ዓመቱ ጀምሮ ፕሮፌሽናል ተጫዋች መሆን ችሏል።
በሕክምና ስራ ላይ የተሰማሩት ወላጆቹ ውድ የሆነውን የቼዝ ጨዋታ ከሀገር ሀገር ተዘዋውሮ እንዲያካሂድ ስራቸውን በማቆም ጭምር ሲደግፉት እደነበርም ተነግሯል።
ከቼዝ በተጨማሪ የተለያዩ ስፖርቶችን እንደሚያዘወትር የሚገልፀው ኮከቡ፤ ስሙን እንደ ማግነስ ካርልሰን ካሉ የቼዝ ቻምፒዮኖች ጋር ማስፈር እንደሚፈልግ ይናገራል።
በአፎሚያ ክበበው
Source(EBC)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe