የሞስኮ እና የቴህራን የምስጢር ሚሳይል ሴራ ይፋ ሆነ

ሩሲያ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካን ግዙፍ የአውሮፕላን ተሸካሚ የጦር መርከቦችን ጨምሮ የሌሎችንም ሀገራት የባህር ኃይል ውቅያኖስ ላይ ለማስቀረት የሚያስችል አደገኛ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ለኢራን በምስጢር እያደለች መሆኑ ተጋለጠ።
«ፋይናንሻል ታይምስ» ያወጣው አዲስ የምርመራ ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ ሞስኮ ለቴህራን የላቁ ሱፐር ሶኒክ (ከድምፅ ፍጥነት በላይ የሚበሩ) የክሩዝ ሚሳይሎችን የመገንባት አቅም የሚሰጥ ጥልቅ የምስጢር ድጋፍ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
ይህ «ሲ430ኤል» በሚል የምስጢር ኮድ ስም የተሰየመውና በ2023 እ.ኤ.አ. ይፋዊ እንቅስቃሴውን የጀመረው ፕሮግራሞች፤ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውን የሩሲያ የሚሳይል ሊቃውንት በዋናነት ያሳተፈ ነው። ድንቅ የሚያደርገው ደግሞ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል ከፍተኛ የጦርነት ውጥረት እና ወታደራዊ ግጭት በነበረበት ወቅት እንኳ ይህ ምስጢራዊ ወታደራዊ ትብብር ለአንዲት ሴኮንድ እንኳ አለመቋረጡ ነው።
የፋይናንሻል ታይምስ የምርመራ ቡድን እጁ ላይ ያስገባቸው አስደናቂ ቴክኒካዊ ሰነዶች የተገኙት ከሚከተሉት አቅጣጫዎች ነው፡
ከሾለኩ የሩሲያ ከፍተኛ የደብዳቤ ልውውጦች ;የሩሲያ ከፍተኛ መሐንዲሶችና ባለስልጣናት የጉዞ መዝገቦች
የጦር መሳሪያዎች የፓተንት (Patent) ጥልቅ ትንተናዎች ነው።
ይህ ክስተት ከሞስኮ ወደ ቴህራን ከተደረጉ የቴክኖሎጂ ዝውውሮች ሁሉ እጅግ ስትራቴጂካዊ፣ አደገኛ እና ታላቅ ወታደራዊ ክስተት ተደርጎ ተወስዷል።
የዚህ ፕሮጀክት ዋና አላማ የክሩዝ ሚሳይሎች ከድምፅ ፍጥነት በበርካታ እጥፍ ፈጥነው እንዲበሩ የሚያስችለውን «ራምጄት» (Ramjet) የተባለውን የላቀ የ ቴክኖሎጂ ለቴህራን ማስተላለፍ ነው።
ቴክኖሎጂው የምድር ላይ ጥቃት እና የባህር ኃይል መርከብ መቺ ሚሳይሎችን ለመስራት የሚያገለግል ነው።
ሚሳይሎቹ ያላቸው እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት ከዝቅተኛ የበረራ ከፍታ ጋር ሲቀናጅ፤ የጠላት የአየር እና የሚሳይል መከላከያ ስርአቶች ሚሳይሉን አየር ላይ አትኩረው ለመምታትና ለማከሸፍ የሚያስችላቸውን የጊዜ መስኮት ሙሉ በሙሉ ይዘጋባቸዋል።
«ይህ ኢራናውያን ለበርካታ አስርት ዓመታት ለማግኘት ሲመኙት የነበረ እና ከሩሲያ የተደረገ ከፍተኛ ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ ዝውውር ነው፤ እንዲህ ዓይነቱ መረሃ ግብር ደግሞ ያለ ሩሲያ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ውሳኔና ፈቃድ በፍጹም ሊከናወን አይችልም።»
ከ2014 ጀምሮ በአሜሪካ ማዕቀብ የተጣለበት ዋና የሩሲያ የሮኬት ዲዛይን ቢሮ ነው።
የሾለኩ የጉዞ መዝገቦች እንደሚያሳዩት ውሉ ከኢራን የመከላከያ ሚኒስቴር ጋር በህዳር 2023 ከመፈረሙ በፊት የሩሲያ ባለስልጣናት እና የሮኬት መሐንዲሶች ወደ ቴህራን ተደጋጋሚ ምስጢራዊ ጉዞዎችን አድርገዋል።
እ.ኤ.አ. በ2025፡ ሩሲያ ከኢራን የተላኩ የራምጄት ስርአት ቴክኒካል መረጃዎችን በመቀበል የበረራ ሙከራዎችን መርምራለች። በተጨማሪም በነዳጅ ስርአት፣ በቃጠሎ ተረጋጋጋነት፣ በአየር ማስገቢያዎች እና ኖዝሎች ላይ ዝርዝር የሙያ መመሪያዎችን ሰጥታለች።
እስከ 2026፡ የዚህ ሁለተኛው ምዕራፍ የቴክኒክ ውይይቶች እና ክትትሎች እስከ 2026 ድረስ በከፍተኛ ጥንካሬ ቀጥለዋል።
ኢራን የራምጄት ሞተር ስርአትን ገንብታ የበረራ ሙከራዎችን ያደረገች ቢሆንም፤ በሩሲያ እገዛ ሙሉ በሙሉ የተገነባ ከድምፅ ፍጥነት በላይ የሚበር የክሩዝ ሚሳይል ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ታጣቂዎች እጅ መግባቱን የሚያሳይ እስካሁን የተረጋገጠ ማስረጃ የለም። ነገር ግን የቴክኖሎጂው ዝውውር የመካከለኛው ምስራቅን ወታደራዊ ሚዛን በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀየረው ይነገራል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe