የሪል ስቴት ውል ከመፈረምዎ በፊት ማስተዋል ያለብዎ 4+ ነገሮች! 

በብዙ ድካም እና ጥረት ያከማቹትን ገንዘብ አውጥተው ሪል እስቴት ለመግዛት ሲያስቡ፣ የያዙት ውል የሕይወት ዘመን እፎይታዎን ወይም ዕድሜ ልክ የሚጸጸቱበትን ድ ሊወስን ይችላል!
ብዙ ሰዎች በብርቁ የቤት ህልማቸው ተይዘው ውል ሲፈራረሙ ትልልቅ የህግ ስህተቶችን ይሰራሉ። ማንኛውንም የሪል እስቴት ውል ከመፈረምዎ በፊት እነዚህ 4+ አደገኛ ነገሮች በውሉ ውስጥ ካሉ በፍጹም እጅዎን እንዳያነሱ!
 1. “በቃል ተስማምተናል” የሚል ማታለል!
“ወንድሜ/እህቴ ይሄን እኮ አሟልተን እንሰጥሃለን!” የሚል የቃል ቃል-ኪዳን ፍርድ ቤት ፊት ምንም ዋጋ የለውም!
እውነታው፡ ችግር ሲፈጠር አሻጭ “በአፌ ተናግሬ ነበር” የሚለውን አያምንም።
መፍትሔ፡ እያንዳንዱ ትንሽ ዝርዝር (ካሬ ሜትር፣ ማጠናቀቂያ ዕቃዎች፣ ፓርኪንግ…) በጽሑፍ ሰፍሮ የሁለቱም ወገን ፊርማ ማረፍ አለበት!
 2. ውሉን አሻጭ ብቻ የሚያሻሽልበት አንቀጽ!
ውል ማለት በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ እኩል ስምምነት ነው።
አደገኛው ነገሮች፡ “ኩባንያው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የውሉን አንቀጾች የማሻሻል መብት አለው” የሚል መስመር ካዩ ወዲያውኑ ውሉን ይቃወሙ!
መፍትሔ፡ ማንኛውም ለውጥ በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ብቻ ሊደረግ እንደሚችል መረጋገጥ አለበት።
 3. “የከፈሉት ገንዘብ አይመለስም” (No Refunds)
ይህ ትልቁ የገንዘብ ወጥመድ ነው!
እውነታው፡ ስህተቱ፣ መዘግየቱ ወይም የውል ማፍረሱ የነሱ እንኳ ቢሆን፣ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ እንዳይሰጥዎት የሚያደርጉበት አድሏዊ ዘዴ ነው።
መፍትሔ፡ ጥፋቱ የሪል እስቴቱ ከሆነ ገንዘብዎ ከነካሳው የሚመለስበት አንቀጽ በውሉ መካተት አለበት።
 4. የማስረከቢያ ጊዜ ገደብ (Deadline) አለመኖር!
“ቤቱ በቅርብ ጊዜ ተሰርቶ ያልቃል…” የሚል አሻሚ ቃል አትቀበሉ!
አደገኛው ነገሮች፡ ትክክለኛ የተወሰነ ቀን፣ ወር እና ዓመት ካልተቀመጠ፣ ለዓመታት ሳይረከቡ ገንዘብዎ ታስሮ ሊጉላሉ ይችላሉ።
መፍትሔ፡ ቤቱ የሚያልቅበት ትክክለኛ ቀን መቀመጥ አለበት፤ እንዲሁም በተቀመጠው ጊዜ ካላስረከቡ አሻጭ ለቀጠሮ መዘግየቱ የቅጣት ክፍያ (Penalties) የሚከፍልበት አንቀጽ መኖሩን ያረጋግጡ!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe