የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች 14 ሚሊዮን ብር ካሳ ሊከፈለው ነው

የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች 14 ሚሊዮን ብር ካሳ ሊከፈለው ነው፡፡ ካሳ ከፋዩ የእግር ኳስ ክለብም የውጭ ሀገር ክለብ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የቀድሞ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች 14 ሚሊዮን ብር ካሳ ሊከፈለው ነው፡፡ የግብጹ የእግር ኳስ ክለብ ለኢትዮጽያዊው ተጫዋች ነው ይህንን ካሳ እንዲከፍል ፊፋ ወስኖበታል ተብሏል፡፡

የግብጹ ሀራስ አል ሆዱድ ክለብ ለሄኖክ አዱኛ ካሳ እንዲከፍል የሚል ውሳኔ ፊፋ ማሳለፉ ታውቋል፡፡

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ተጫዋች የነበረው ሄኖክ አዱኛ ለግብጹ ሀራስ እግር ኳስ ክለብ በመፈረም አቅንቶ የነበረ ሲሆን አንድም ጨዋታ ላይ ባለመሰለፉ የነበረውን ስምምነት አፍርሶ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

ሄኖክ በግብጹ ቆይታው አንድም ጨዋታ ላይ ያልተሰለፈ ሲሆን ደመወዝም ሳይከፈለው ቆይቷል ጉዳዮንም ወደ ፊፋ ወስዶት ክስ መስርቶ ነበር፡፡
የፊፋ እግር ኳስ የግልግል ኮሚቴው በሰጠው ውሳኔ የግብጹ ክለብ የተጫዋቹን ደመወዝ 12ሺ 197 ዶላር ከ19 ሳንቲምና ተጨማሪ 5 በመቶ ወለድ እንዲከፈለው ተወስኗል፡፡

በተጨማሪም ክለቡ ከተጫዋቹ ጋር የነበረውን ውል በማቋረጡ 94ሺ 926 ዶላር ካሳ እንዲከፈለው ተወስኗል፡፡ ሄኖክ በአሀኑ ስዓት ለመቀሌ 70 እንደርታ ተሰልፎ እየተጫወተ ይገኛል፡፡/

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe