የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች በጨረታ የሚያቅርበውን የውጭ ምንዛሪ በቋሚነት የማያቀጥል መሆኑን አስታወቀ።
በቅርቡ በተካሄደው የፋይናንስ ፎረም ላይ የተገኙት የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ቺፍ ኢኮኖሚስት አቶ ፈቃዱ ደግፌ እንደገለጹት፣ የባንክ ሥርዓቱ በራሱ መቆም በመጀመሩ ምክንያት ባንኩ በጨረታ የሚያቀርበው የውጭ ምንዛሪ ቀሪ ሊሆን ይችላል። በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በባንክ ሥርዓቱ በኩል ለገቢ ንግድና ሌሎች ግዥዎች ከ17 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ የብሔራዊ ባንክ ጨረታ ድርሻ 17 በመቶ ብቻ ነበር። ይህም ባንኮች በራሳቸው መንገድ የሚያገኙት የውጭ ምንዛሪ የንግዱን ማኅበረሰብ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ማሟላት መጀመሩን ያሳያል።
ወደፊት ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ገበያው ውስጥ የሚኖረው ሚና የመሠረታዊ ዕቃዎች አቅርቦትን በጊዜያዊነት መደገፍ፣ አላስፈላጊ የምንዛሪ መዋዠቅን (Volatility) ማስወገድና የምንዛሪ መረጋጋትን መፍጠር እንደሆነ ተብራርቷል።
በተጨማሪም የብር ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ቀደም ሲል ይሠጋ እንደነበረው የዋጋ ግሽበትን ሳይሆን፣ በተቃራኒው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ቅናሽ እንዲመዘገብ ማስቻሉን የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና የብሔራዊ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች አስረድተዋል።
የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ በቋሚነት እንደማይቀጥል ተገለጸ

