የተቆጣ በሬ ባለቤቱን ወግቶ መግደሉን የኮንታ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

ነገሩ እንዲህ ነዉ በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ ኮንታ ገነት ቀበሌ ነዋሪ አቶ ፍቃዱ ማሞ አንድ የእርሻ በሬ አላቸዉ እሳቸዉ ሻኛዉን እያሹ ቀንበር ከጫንቃዉ በማድረግ ከሌላኛዉ በሬ ጋር ጠምደዉ ያርሱበታል።
የበሬዉና የአቶ ፍቃዱ እርሻ ካላቸዉ ጠምደዉ እያረሱ እርሻ ሳይኖር ሲቀር በሬዎቻቸዉን ጥሩ ሳር ያለበት እያሰሩ ይንከባከቧቸዋል።
ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5:30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በሬዉ ያለወትሮዉ ይጮኸል ጥሩ ሳር ወዳለበት ቀይሩኝ በሚል ድምፁን እየሰሙ የነበሩት አቶ ፍቃዱ የታሰረበትን ገመድ ፈተዉ ሻኛዉን ለመዳበስ ሲሞክሩ በሬ ተቆጣ ተቆጥቶም አላበቃም ግለሰቡን በቀንዱ ወጋቸዉ።
መሬት ለመሬት እያንከባለለ በእግሩ መሬቱን እየጫረ በቀንዱ እያነሳ ከመሬት ያፈርጣቸዉ ጀመር።በድንጋጤ የተዋጡት አድኑኝ ሲሉ ተጣሩ ቤተሰቡ ከያለበት ወጣ በሬዉ ቁጣዉ በረታ ደጋግሞ መዉጋቱን ቀጠለ ግለሰቡ ድምፅ አላሰሙም።
መንደርተኛዉ ተሰባስቦ በሬዉን በድንጋይ በዱላ አባረሩት ተጎጂዉ ህይታቸዉ አለፈ።
ጉዳዮ ፖሊስ ዘንድ መረጃዉ ደረሰ ፖሊስ ደርሶ ህ/ሰቡን አስተባብሮ በሬዉ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርስ ተደርጎ ከበረት እንዲዉል ተደረገ። ፖሊስ አንዳንድ ጊዜ የምናሳድጋቸዉ የቤት እንስሳት ዉሻ፣ድመት በግና በሬ የመቆጣት ባህሪ ስለሚያሳዩ ህዝቡ ሁሌም መጠንቀቆ ይኖርበታል ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል መረጃዉ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነዉ።
ፎቶ:-ከማህበራዊ ሚዲያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe