የአልኮል መጠጦች በማህበራዊ ሚዲያ እንዳይተዋወቁ የሚከለክል ረቂቅ ደንብ ሊጸድቅ ነው

ረቂቅ ደንቡን ፍትህ ሚኒስቴር ከተመለከተው በኋላ ወደ ሚኒስትሮች ም/ቤት ተመርቷል ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጽያ ምግብና መድሃኒት አስተዳደር  አዋጅ ቁ 1112/2100 ከመጽደቁ በፊት የአልኮል ምርቶች ማስታወቂያ እንደ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙሃን በስፋት ይሰራጭ እንደነበርና አዋጁ ከጸደቀ በኋላ ማንኛውም የአልኮል ምርት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በመደበኛ መገናኛ ብዙሃን ሙሉ በሙሉ መከልከሉን ባለስልጣኑ አስታውሷል፡፡በዚህም በርካታ ሚዲያዎቸ በበጀት እጥረት መዝጋታችውና ጋዜጠኞቻቸውን መበተናቸው ታውቀል፡፡

በመደበኛ መገናኛ ብዙሃን ይሰራጭ የነበረው የአልኮል ምርቶች ማስታወቂያ በአዋጅ መታገደቡን ተከትሎ የአልኮል አምራች ተቋማት በማህበራዊ ሚዲያ ማስታዋወቅን እንደ አማራጭ እየጠቀሙበት ነው ተብሏል፡፡

በመሆኑም የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ማስተዋወቅን የሚከለክል ረቂቅ ደንብ ነው ወደ ሚኒስትሮች ም/ቤት ተመርቷል የተባለው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe