ኢትዮጵያ ኤችአይቪን ለመከላከል በአመታት ልፋት ያገኘቻቸው ውጤቶች ወደኋላ እንዲመለሱ መፍቀድ የለብንም ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አሳሰበ። ለዚህም የሚቻለኝን እያደረኩ ነው ብሏል።
በአመታት ልፋት በኢትዮጵያ ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል የተደረጉ ጥረቶች ከፍተኛ ውጤጥ አስመዝግበው እንደነበር በመግለጽ በድንገት ድጋፍ እና እርዳታ መቋረጡ ተጽእኖው አስጊ ነው ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት የኤድስ ድጋፍ (ዩኤን ኤድስ) የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ቲና ቡንቶ አስታውቀዋል።
“ወትሮም ደካማ በሆነው የሀገሪቱ የጤና ሲስተም ላይ ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር ነው” ሲሉ አሳስበዋል።
አብዘሃኛዎቹ በኢትዮጵያ የሚገኙ የኤችአይቪ ኤድስ ህሙማን መድሃኒት የሚወስዱት ከአለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች በተገኘ ድጋፍ መሆኑን አስታውቀዋል።
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ህሙማን የሚሰጠው ድጋፍ መቋረጡን ተከትሎ የሚፈጠረው ክፍተት በመንግስት አና በማህበረሰቡ እንዲሸፈን ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ማካሄዱን ዋና ዳይሬክተሯ አመላክተዋል።/

