የአሜሪካ እና የኢራን ውጥረት አደገኛ ወደሆነ ምዕራፍ ተሸጋገረ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ አዲስ እና ተጨማሪ የአየር ጥቃቶችን ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ እርምጃው “ኢራንን አስገድዶ ወደ ድርድር ጠረጴዛ የማምጣት ዓላማ የለውም” ሲሉ በይፋ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ ‘ትሩዝ ሶሻል’ በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መግለጫ፣ አሜሪካ በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ላይ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ቁጥጥር ማድረጓን ጠቁመው፣ “የኢራን መንግስት የማይቀረውን ውድቀት እየተጠባበቀ ነው፤ የኢራን ህዝብ ተነስቶ የሚታገለው መቼ ነው?” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) በ’ኤክስ’ ገጹ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኢላማ ያደረገው የቴህራንን የአየር መከላከያ፣ የግንኙነት ጣቢያዎች እና የራዳር ስርዓቶችን እንደሆነ አስታውቋል። ይህ እርምጃ የተወሰደው ኢራን በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች እና በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ያደረገችውን የጥቃት ሙከራ ለመበቀል መሆኑም ተገልጿል። ትራምፕ አክለውም፣ ቴህራን አጸፋዊ እርምጃ የምትወስድ ከሆነ አሜሪካ የበለጠ “ግዙፍ እና ኃይለኛ” ወታደራዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝተዋል።
ኢራን በበኩሏ ለአሜሪካ ጥቃቶች በወሰደችው የአጸፋ እርምጃ የአሜሪካ አጋር የሆነችውን ዮርዳኖስን ዒላማ አድርጋለች። የዮርዳኖስ የጦር ኃይሎች ከኢራን ግዛት የተተኮሱ 13 ሚሳኤሎች እንደደረሱባቸው ያረጋገጡ ሲሆን፣ 10ሩ በአየር መከላከያ ስርዓት ሲከሸፉ ቀሪዎቹ 3ቱ ራቅ ባሉ አካባቢዎች ላይ ወድቀዋል። እስካሁንም የተመዘገበ የሰው ጉዳት የለም።
በተመሳሳይ ጊዜ የባህሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ሊከሰት የሚችል የጸጥታ ስጋት ማስጠንቀቂያ በማውጣት፣ ዜጎች ወደ አስተማማኝ መጠለያ እንዲያመሩ አሳስቧል።
ይህ ወታደራዊ ግጭት በዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያ ላይ ስጋት ፈጥሯል፡የብሬንት (Brent) ነዳጅ ዋጋ: በ4.5 በመቶ በማደግ በርሜሉ 94.52 ዶላር ደርሷል።
የዌስት ቴክሳስ (WTI) ነዳጅ ዋጋ: በ5 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 90.03 ዶላር በመሸጥ ከሐምሌ ወር ወዲህ ከፍተኛውን ደረጃ ይዟል።
ይህ የጥቃት ልውውጥ እሁድ ዕለት አሜሪካ በኢራን ላራክ ደሴት በሚገኙ የሮኬት ማስወንጨፊያዎች ላይ ጥቃት በመክፈቷ የተጀመረ ሲሆን፣ ሰኞ ዕለት የኢራን ኃይሎች በዮርዳኖስ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ አጸፋዊ ጥቃት ፈጽመው ነበር። የትራምፕ አስተዳደር በቴህራን ደጋፊዎች ላይ የጣለውን ጠንካራ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ተከትሎ፣ ቀጠናው ወደ ከፋ ወታደራዊ ግጭት ያመራል ወይ የሚለው የዓለም ስጋት ሆኗል።//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe