የዩናይትድስቴትስ ጦር ሰኞ እለት አደንዛዥ እፅ በመዘዋወር በጠረጠራቸው ሦስት ጀልባዎች ላይ ጥቃት አድርሶ 8 ሰዎችን በምስራቃዊ የፓሲፊክ ውቂያኖስ አካባቢ ገድሏል።
አሜሪካ እንዳለችው ከሆነ ሦስቱም ጀልባዎች በእፅ ዙውውር ላይ ተሳታፊዎች ናቸው። ይሄው የሰኞው ጥቃትም ወደ አሜሪካ በህገ ወጥ መንገድ የሚገባውን የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን ለመግታት የተጀመረው የዘመቻው አካል ነው።
አሜሪካ የአደንዛዥ እፅ ዝውውርን እየተዋጋሁ ነው በትልም ከወቀሳ ግን አልዳነችም።
ጦሩ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው በተለዩ ሽብርተኞች ላይ መሆኑን ተናግሯል።
በመጀመሪያው ጀልባ ላይ ሦስት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፡በሁለተኛው እና በሦስተኛው ጀልባ ላይ ደግሞ ሦስትና ሁለት እፅ አዘዋዋሪዎች እንደተገደሉ የጦሩ መግለጫ አሳውቋል።
የፕሬዘዳንት ትራምፕ አስተዳደር ከመስከረም አንስቶ ተለይተው በተነገሩ 25 የሚሆኑ ጥቃቶች ሳቢያ ከዚሁ ከእፅ ጋር በተገናኘ እጃቸው አለበት የተባሉ 95 ሰዎች ተገድለዋል።
በዚህ የአሜሪካ ዘመቻ ምክንያት ሀገሪቱ ከቬኔዙዌላ ጋር ወደ ፍጥጫ አምርታ ቀጥላለች።//
የአሜሪካ ጦር በፓሲፊክ በሦስት ጀልባዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ስምንት ሰዎችን መግደሉን አስታወቀ

