የአርቲስት መሐሙድ አህመድ የሙዚቃ ህይወቱ የመጨረሻ ኮንሠርት ሊደረግ ነዉ

ዘመናዊ ሙዚቃን ከባህላዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ጋር አዋህዶ በመዝፈን በአገራችን ቀደምት የሙዚቃ ንጉስ የሆነዉ አርቲስት የክብር ዶክትር ማሕሙድ አሕመድ ክብር ይገባዋል በማለት አድናቂዋቹ እና ወዳጆቹ በመሰባሰብ ኮሚቴ በማዋቀር ላለፉት ሁለት አመታት የተለያዩ ስራዋችን ሲሰሩ ቆይተዋል፤
1. የጋሽ ማህሙድን የመጨረሻ የሙዚቃ መድረክ ማዘጋጀት
2. የጋሽ ማህሙድ የህይወት ታሪክ መጽሃፍ ህትመትና ምረቃ
3. በጋሽ ማህሙድ ስም መንገድ / አደባባይ ማሰየም
4. የጋሽ ማህሙድን ሃውልት ማቆም ይገኙበታል ከነዚህም የክብር ስራዋቹ ዋነኛው ስራ የጋሽ ማሕሙድን የመጨረሻ የስንብት የሙዚቃ ኮንሰርት ማዘጋጅት ለዚህም ኮንሰርት ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከጋሽ ማህሙድ ኮሚቴ ጋር የውል ስምምነት ገብቶ ሙሉ ሃላፊነት ተቀብሎ ይህንን የመጨረሻ የሙዚቃ መድረክ ለማዘጋጀት በጋራ ቀን ቆርጠናል፡፡
ቀኑም ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ሲሆን በእለቱም እስከ 25,000 ታዳሚያን ይገኛሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ጆርካ ኢቨንት ላለፉት 10 አመታት ኮንሰርቶችንና የተለያዩ ኢቨንቶችን በአገር ውስጥና በውጭ ሃገር በማዘጋጀት በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ያካበተ ድርጅት ነው፡፡ጋሽ ማሕሙድ በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በሊይ ከልጅነቱ አንስቶ የአገራችንን ሙዚቃ በተለያዩ የአገራችን ቋንቋዎች በመዝፈን፣ የአገራችንን ሙዚቃ ከአገር አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲደመጡ ያበረከተው አስተዋጽኦ ለአሁኑ ትውልድ ትልቅ አርአያ የሆነ የሙዚቃ ንጉስ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እ.አ.አ በ2007 ቢቢሲ ሬዱዮ ከአፍሪካ በድንቅ ዘፋኝነቱ “BBC Radio World Music Award”ተሸሊሚ አድርጎታል፡፡በአገራችንም መቼም የጋሽ ማሕሙድን ሙዚቃ እያጣጣመ ያላደገ ሰው አለ ብለን አንገምትም፡፡
ጋሽ ማሐሙድ ለአገራችን የሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክተር ማዕረግን ሰጥቶታል፡፡ይህ በአገራችን የሙዚቃ ዘርፍ ስመጥር ሀብታችን የሆነውን የሙዚቃ አባት ከሙዚቃ አለም ለመሰናበት ወይም ማይኩን ሊሰቅል ሲዘጋጅ እጃችንን አወዛውዘን መሸኘት አግባብነት የለውም በሚል ሽኝቱን በደመቀ እና በታሪክ ማስታወሻነትም እንዲቀመጥ ጆርካ ኤቨንት ይህን ከባድ ኃሊፊነት ከጋሽ ማሕሙድ ኮሚቴ በመረከብ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ደረጃውን የጠበቀ የመጨረሻውን የህይወት ዘመን ስንብት ኮንሰርት  እንደሚካሄድ በሸራተን ሆቴል በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጣል፡፡ እንዱሁም በዚህም ቀን በክብር ዶ/ር አርቲስት ማሕሙድ አሕመድ የሙዚቃ ሕይወት የተዘጋጀ መፅሀፍ የሚመረቅ ይሆናል፡፡ ያሉት ኮሚቴዎቹ ይህም የመጨረሻ የመድረክ ስንብት ሁሉም ኢትዮዽያዊ ከጎናችን ይቁም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe