የአውሮፓ ሀገራት በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ የሚያደርጉትን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸው ተነገረ

አሜሪካንን ጨምሮ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ለረጅም ዓመታት በኢትዮጽያ በጤናው ዘርፍ ላይ ያደርጉ የነበረውን ድጋፍ በድንገት ሙሉ በሙሉ ማቋረጣቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጽያ ተወካይ ዶ/ር አወቀ ጣሳው ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል፡፡

ውሳኔው በድንገት የሆነ መሆኑን አንስተው በጤናው ዘርፍ ላይ የሚታየውን ችግር ውስብስብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ኢትዮጽያ ለረጅም ዓመታት በጤናው ዘርፍ አንድ ሦስተኛውን ድጋፍ ታገኝ የነበረው ከለጋሽ ሀገራት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

መንግስት ይህንን ከግንዛቤ በማስገባትም ዘርፉ ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቋቋም ዝግጅት ማድረግ እንደሚኖርበት ተመላክቷል፡፡

ሀገራቱ ለኢትዮጽያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያቋርጡ ያስገደዳቸውም የሰሞንኛው የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውጥረት እና ዓመታትን የተሻገረው የሩሲያና የዩክሬነኑ ጦርነት ስጋት በመደቀኑ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

የኢትዮጽያ መንግስት ይህንን ድንገተኛ ውሳኔ በትኩረት በማየት የሀገር ውስጥ የፋይናስ ተቋማትን አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ማበረታት እንደሚጠበቅበት የመንግስታቱ ድርጅት የድጋፍ አስተባባሪ የኢትዮጽያ ተወካይ ጥሪ አቅርቧል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe