የአዲስ አበባ ነጋዴዎች የሂሳበ መዝገብ ተቀባይነት አጣ

ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ ነው ተብሏል፡፡ 75 ከመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ነጋዴ የሂሳብ መዝገቡ ተቀባይት እንደሌለው የገለጸው የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ ነው፡፡

ቢሮው 25 ከመቶ የሚሆኑ ነጋዴዎች ብቻ የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ማገኘቱን ገልጻል፡፡ ቀሪቆቹ 75 በመቶ የሚሆኑት ያቀረቡት የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀ እና ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች የተዘጋጀ ባለመሆኑ ተቀባይነት አላገኘም ብላል፡፡

ነጋዴዎች የሚያቀርቡት የሂሳብ መዝገብ በባንክ ሂሳባቸው ከሚንቀሳቀሰው ገንዘብ ጋር የማይጣጣም ነው፡፡ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በባንክ አካውንታቸው ላይ ቢታይም በሂሳብ መዝገባቸው ላይ ምንም ትርፍ እንዳላገኙ ያሳያሉ ነው ያለው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ገንዘቡን በህጋዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ወጭ አድርገው ማስረጃ ማቅረብ አይችሉም ተብሏል፡፡//

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe