የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት መምህርና ታላቅ የሥነ ጥበብ ሰው በኃይሉ በዛብህ አርብ ሚያዝያ 02/08/2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም በድንገት አርፏል።
በኃይሉ በዛብህ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ዘመናዊ የሥነ ጥበብ እንቅስቃሴ ውስጥ የተደላደለ ስፍራ የያዘ፣ ምሳሌ መሆን የቻለ፣ ጥንቅቅ ያለ ሙያተኛና መምህር ነበረ።
በቀድሞው የሥነ ጥበባት ኮሌጅ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተባባሪ ዲን ሆኖ አገልግሏል። የሥነ ጥበብ ረዳት ፕሮፌስር ሲሆን፣ በተማሪዎች፣ በመምህራን እና በሥነ ጥበብ ማኅበረሰቡ ዘንድ እጅግ የሚደነቅና የሚወደድ ሰው ነበረ።
የአቶ በኃይሉ በዛብህ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ አርብ ሚያዝያ 02/08/2018 በኮተቤ ሐና ወእያቄም ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተፈጸማል።

