የአፋር ክልል መልክዓ ምድርን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ኢትዮጵያ የአፋር ክልል መልክዓ ምድርን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ ዝርዝር ውስጥ ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ ጀመረች
 እውቅናው በምድር በጣም ልዩ ከሆኑ የመሬት አቀማመጦች አንዱን ለመጠበቅ እንዲሁም ቱሪዝምና የአካባቢው ነዋሪዎችን ኑሮ ለመደገፍ የሚያስችል ነው።
ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫና የማስጀመሪያ መርኃ-ግብር በሰመራ ከተማ ተካሂዷል።
ከክልሉ ተፈጥሯዊ ገጽታዎች በጥቂቱ፦
⚡️ የደናክል አዘቅት፦ (ከባሕር ወለል በታች 125 ሜትር የተለካ)፣
⚡️ ኤርታ አሌ፦ በዓለም ላይ ካሉ ጥቂት የማይነጥፍ እና ሁልግዜ የሚፈላ የላቫ ሐይቅ ያለው እሣተ ጎመራ፣
⚡️ ሀደራ፦ 3.2 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላት ቀደምት የሰው ልጅ ዘመድ ድንቅነሽ (ሉሲ) የተገኝችባት ሥፍራ።

🤝 ተሳታፊዎች የክልሉን ሥነ-ምድራዊ ገጽታዎች፣ የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ታሪክ እና የባሕል እሴቶች በስርዓት መመዝገብ፣ መመርመርና መጠበቅ እንዳለባቸው ተስማምተዋል።

Sourcesputnik

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe