የኢራን እና አሜሪካ ስምምነት ጊዜ ማብቃቱን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ አሻቀበ

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ የመግባቢያ ስምምነት ጊዜ ማብቃቱን ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
በሁለቱ አገሮች መካከል በሰኔ ወር የተፈረመው ስምምነት ሰኞ ዕለት ጊዜው ማብቃቱ ተገልጿል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስምምነቱን ጊዜ ለማራዘም የሚደረግን ውይይት ውድቅ አድርጓል።
የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ካልተሳካ ተከላካይ ብቻ ሳይሆኑ ወደ ማጥቃት እንደሚሸጋገሩ አስጠንቅቀዋል።
ይህንን ተከትሎ የአሜሪካ ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በበርሜል 82.79 ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ መለኪያው የሆነው ብሬንት በበርሜል 89.06 ዶላር ደርሷል።
የሁለቱ አገሮች ስምምነት የሆርሙዝ ሰርጥን ክፍት ለማድረግ ያለመ ነበር። ሆኖም አሜሪካ ስምምነቱን ጥሳለች በሚል ኢራን ተጨማሪ ውይይት እንደማታደርግ አስታውቃለች። የዚህ ውጥረት መጨመር በአለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል።

Sourcedere tube

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe