የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ስርዓተ ቀብርተፈፀመ

የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ።

የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ስርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈፅሟል።

ስርዓተ ቀብር የተፈፀመው ቤተሰቦቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው የሙያ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም የመንግስት ባለስልጣናትና የተለያዩ ተቋማት መሪዎች በተገኙበት ነው።

ከስርዓተ ቀብር ስነስርዓቱ ቀደም ብሎ የስንብት መርሃ ግብር በአድዋ ሙዚየም  ተካሂዷል። አቶ አማን ፍስሃጽዮን የኢትዮጵያን የሚዲያ ኢንዱስትሪ በማዘመንና ጥበብን ወደ ቤታችን በማድረስ ረገድ የማይረሳ አሻራ ጥለው አልፈዋል። ላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ ሁሌም ሲታወሱ ይኖራሉ።

በድጋሚ ለአቶ አማን ፍስሃፅዮን ቤተሰቦች፣ የሥራ ባልደረቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ቤተሰቦች ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትስስር ይፍጠሩ

325,851FansLike
49,039FollowersFollow
13,194SubscribersSubscribe