ግዙፉና መንግሥታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ አክስዮን ሽያጭ 100 ሚሊዮን አክሲዮኖችን ማቅረቡን አስታውቋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያውያን ክፍት የተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ ዝቅተኛው የሼር ወይም የአክሲዮን መጠን 33 እንዲሆን የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንዲሆን መወሰኑን የገለጸ ሲሆን፤ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች ለሽያጭ መቅረባቸውን ገልጿል፡፡
ከፍተኛው የክሲዮን ወይንም የሼር መጠን 3 ሺሕ 333 እንደሆነና የአንዱ አክሲዮን ዋጋም 300 ብር እንደሆነ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
የአክሲዮን ሽያጩ ከዛሬ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ በአክስዮን ሽያጩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ለሽያጩ ከማመልከታቸው በፊት ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅደመ-ሁኔታዎች መካከል፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆን እንደግዴታ ተቀምጧል።
ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ መቆየቱ ይታወቃል።

