ዛሬ በአድዋ ሙዚየም ሀገራዊ የስፖርት ልማት ስብራቶችን በሳይንሳዊ ጥናት እንፍታ በሚል የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ጥናት ነው ጉዳዩ የቀረበው።
በጥናቱ ሀገራዊ የስፖርት ምክር ቤት በተሻሻለ ደንብና መመሪያ ለማቋቋም በቀረበ ጥናት ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖችን ጉዳይ በልዩ ክፍል የቀረበው።
የስፖርት ምክር ቤት ጽ/ቤቱ ሲደራጅ በቀጥታ ከፌዴሬሽኖች የተመረጠ ባለሙያ በምክር ቤቱ ሀላፊነት በምክትል ሊ/ መንበር እንዲሾምና በቀጥታ የብሄራዊ ቡድን ጉዳይ ክትትል እንዲደረግ የሚደረግበት ነው ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፋይናንስ ችግሮችና የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን በመጥቀስ መንግስት ብሄራዊ ቡድኑን እንዲረከብ ጥያቄ ከማቅረብ ተጨማሪ የአ.አ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤን የበላይ ጠባቂ እስከማድረግ መድረሱ ይታወሳል ።
ባላገሩ ስፖርት

